በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸው መንደሮች ፋይዳ ቢስ ናቸው አለ


ቤልግሬድ 2016
ቤልግሬድ 2016

ሩሲያ በዚህ ወር የተቆጥጠረቻቸው ሁለት ዩክሬን መንደሮችን መኖራቸውን የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ቅዳሜ ያስታወቀ ሲሆን ነገር ግን ሁለቱም ከወታደራዊ ስልት አኳያ መልኩ 'ኢምንት' ናቸው ብሏል።

ቬሴል የተባለች በባክሙት አቅራቢያ የምትገኝ ትንሽ መንደር ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 102 ሰዎች ይኖሩባት የነበረች ሲሆን በካርኺብ አቅራቢያ የምትገኘው ክሮክማልኔ ደግሞ 45 ነዋሪዎች ነበሯት።

ሩሲያ አነስተኛ እና ጥቃቅን መንደሮችን መያዝ መቀጠሏ፤ ‘ዩክሬን መከላከያዋ ላይ ስታተኩር የሩሲያን ጥቃቅን ገድሎችን መሻት’ አመላካች ነው ሲል ጨምሮ አስታውቋል።

በሌላ በኩል የቻይናው ፕሬዘዳንት ዢ ጂንፒንግ የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነትን በተመከተ በስዊዘርላንድ በሚደረገው ‘የሰላም የመሪዎች ስብሰባ’ ላይ እንዲገኙ ዩክሬን ግብዣ አቅርባለች።

በአንጻሩ የሩሲያ አጋር የሆነችው ቻይና ሀገራት ሉዓላዊነትን እና የድንበር ህጎችን ማክበር ይገባቸዋል ስትል ያሳሰበች ሲሆን ይሁን እንጂ በቀጥታ ሞስኮን ከመተቸት ተቆጥባለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG