በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ከ60 በላይ ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጡ


ወደ አውሮፓ በመሻገር ላይ ያሉ ፍልሰተኞች (ፎቶ ፋይል፣ ኤፒ)
ወደ አውሮፓ በመሻገር ላይ ያሉ ፍልሰተኞች (ፎቶ ፋይል፣ ኤፒ)

ፍልሰተኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ተገልብጦ፣ ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ60 ሰዎች በላይ ሞተዋል ሲል የተመድ የፍልሰተኞች ድርጅት አስታውቋል።

ትናንት ቅዳሜ የደረሰው አደጋ፣ ወደ አውሮፓ ለመሻገር በሚሹ ፍልሰተኞች ላይ በሜዲትሬንያን ባሕር ላይ በቅርቡ ከደርሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተብሏል።

የተመድ ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) እንዳለው፣ 86 ሰዎችን ይዞ ትጓዝ የነበረችው ጀልባ፣ ከፍተኛ ማዕበል ገጥሟት በሊቢያ ምዕራባዊ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው ዙዋካ ከተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ስትገለበጥ፣ 61 ሰዎች ሰምጠዋል።

ማዕከላዊው የሜዲትሬንያን ባሕር፣ ለፍልሰተኞች አደገኛ የጉዞ መሥመር መሆኑ ቀጥሏል ብሏል ድርጅቱ በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈረው መልዕክት።

ሊቢያ በጦርነት በመታመስ ላይ ያለች አገር ብትሆንም፣ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ሁከትን እና ድህነት በመሸሽ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚፈልጉ ፍልሰተኞች ተመራጭ መተላለፊያ ሆናለች፡፡

የፍልሰተኞች ድርጅቱ እንደሚለው፣ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈርንጆች 2023 ብቻ፣ ከ2ሺሕ 500 በላይ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በባሕር ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG