በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእንግሊዝ እና የጀርመን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ


የእንግሊዙ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዳቪድ ካሜሮን (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)
የእንግሊዙ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዳቪድ ካሜሮን (ፎቶ ፋይል፣ ኤኤፍፒ)

የእንግሊዙ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዳቪድ ካሜሮን እና የጀርመኑ አቻቸው አናሌና ቤርቦክ፤ በጋዛ ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ በእንግሊዝ በሚታተመው ሰንዴይ ታይምስ ጋዜጣ ላይ በጋራ ባወጡት ጽሑፍ ጠቅይቀዋል።

መደረግ የሚችለው ሁሉ ተደርጎ ተቅኩስ አቁም በአስቸኳይ እንዲፈጸም ሁለቱ ዲፕሎማቶች ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው በቴሌቭዥን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት፣ ጦርነቱ በድል እስከሚጠናቀቅ መደረግ ያለበት የህልውና ጦርነት ነው ብለዋል። “ጋዛ ከሐማስ ወታደራዊ አገዛዝ ወጥታ ፀጥታዋ በእስራኤል ቁጥጥር ሥር እስከሚሆን ይቀጥላል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ባለፈው ዓርብ በስህተት ተገድለዋል በተባሉት ሶስት እስራኤላዊ ታጋቾች ሞት የሰማቸውን ሃዘንም ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞች በሺፋ ሆስፒታል ትናንት ቅዳሜ ሥራ ማከናወናቸውን ድርጅቱ አስታውቋል። መድሓኒት፣ የቀዶ ጥገና ቁሳቁሶችና ሌሎችም የሕክምና ዕቃዎችን እንዳበረከቱ ታውቋል።

በሌላ በኩል፣ ከአንድ የሕፃን መኝታ ቤት ጋር የተገናኘ የሐማስ የምድር ውስጥ መተላለፊያን ማግኘቱን የእስራኤል ጦር በምስል አስደግፎ ይፋ አድርጓል። መተላለፊያውን ያሚያሳየው ቪዲዮም በመረጃ መረብ ላይ ተለቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG