በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ የጦር ኃይል በጎርፍ ከተጎዱ አካባቢዎች ነዋሪዎችን  እያወጣ ነው


የኬንያ ጎርፍ
የኬንያ ጎርፍ

የኬንያ ጦር በጎርፍ አደጋው መውጫ ያጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ለማውጣት የያዘውን ጥረት ዛሬ ሀሙስ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ባለፈው ህዳር ወር የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው እና በርካታ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ባጥለቀለቀው ጎርፍ “በትንሹ 170 ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ600,000 በላይ የሚሆኑ ተፈናቅለዋል ሲል” የነፍስ አድን ጥረቶችን በማስተባበር ላይ የሚገኘው ቀይ መስቀል አስታውቋል፡፡

የረድኤት ድርጅቶች በ100 ዓመታት ውስጥ ታይቶ አይታወቅም ባሉት የጎርፍ አደጋ፣ በሰሜናዊ ኬኒያ ውስጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፣ እንስሳት፣ የእርሻ መሬቶች እና መኖሪያ ቤቶቻቸውን አጥተዋል።

አንድ ዓለም አቀፍ የሳይንቲስቶች ቡድን ባለፈው ሳምንት እንዳለው፣ በሰው ሠራሽ ምክንያቶች የተፈጠረው የአየር ንብረት ለውጥ፣ በምስራቅ አፍሪካ እየጣለ ያለው ዝናብ በሁለት እጥፍ የበለጠ ከባድ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

የኬንያ የአየር ሁኔታ ትንበያ መ/ቤት አዲሱ የአውሮፓውያኑ 2024 ከገባም በኋላ ከባዱ ዝናብ እንደሚቀጥል አስጠንቅቋል።

በቆላማ እና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡም መ/ቤቱ አሳስቧል።

ከአንድ ዓመት በፊት በተከሰተው ከባድ ድርቅ ብዙ ማህበረሰብ አባላት ነዋሪዎችን ህይወት የጠፋበትን የማንዴራ ወረዳ ትናንት ረቡዕ የጎበኙት የብሪታኒያ ከፍተኛ ኮሚሽነር ኒል ዊጋን "የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ላይ በሁሉም ላይ የተደቀነ ተግዳሮት ነው” ብለው “ሆኖም እንደ ሰሜናዊ ኬንያ ባሉ አካባቢዎች ያለውን ድርቅ እና እየሞቱ ያሉ ከብቶችን አሁን ደግሞ የሚታየው የጎርፍ መጥለቅለቅ በሰዎች አኗኗር ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ እጅግ በጣም ትልቅ ነው” ብለዋል፡፡

ኮሚሽነሩ “በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሚከሰቱ ጉዳቶች የገንዘብ ድጋፍ፣ መድሃኒትና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶችን አስመልክቶ ምን ማድረግ እንዳለብን ብቻ ሳይሆን በሀገር አቀፍም ሆነ ዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥ ቀውሶችን ተጽእኖ ለመቋቋም ምን ዓይነት ስርዐቶችን መገንባት እንችላለን የሚለውንም ጨምሮ ሁለቱንም ለማየት ቁርጠኞችን ነን” ማለታቸውን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG