በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዮርዳኖሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ እስራኤል በሐማስ ላይ “የጦር ወንጀል” እየፈጸመች ነው አሉ


የዮርዳኖሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ (ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ)
የዮርዳኖሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ (ፎቶ ፋይል፣ ሮይተርስ)

የዮርዳኖሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ እስራኤል በሐማስ ላይ የምታካሂደውን ጦርነት፣ በፍልስጤማውያን ላይ የተፈጸመ “ግልጽ ጥቃት” እና “የጦር ወንጀል” ሲሉ ገልጸው፣ ሰፊውን የመካከለኛው ምሥራቅ ክልል እንዳያዳርስ ስጋት ደቅኗል ብለዋል።

አይማን ሳፋዲ፣ እስራኤል ጋዛን ከበባ ውስጥ በማቆየት እንዲሁም ምግብ፣ ውሃ እና መድሓኒት እንዳይገባ በማድረግ “የጦር ወንጀል” ፈጽማለች ብለው መናገራቸው፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት እየተበላሸ መምጣቱን አመላካች ነው ሲል አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

እስራኤል ለዮርዳኖሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አስተያየት መልስ አልሰጠችም።

ባህሬን ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለና በጸጥታ ጉዳዮች ላይ ባተኮረ ጉባኤ ላይ የተናገሩት አይማን ሳፋዲ፣ የእስራኤል ጦርነት ጋዛ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በቀጠናው ላይ የሚያስከትለውን አደጋ በተመለከት ሁሉም በግልጽ ሊናገር ይገባል ብለዋል።

“ይህ ራስን መከላከል ሳይሆን፣ ግልጽ ወረራ ነው። ሰለባዎችም ንጹሃን ፍልስጤማውያን ናቸው” ሲሉ አክለዋል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG