በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳልማን ሩሽዲ በጀርመን ተሸለመ


ሳልማን ሩሽዲ (ፎቶ ፋይል፣ ኤፒ)
ሳልማን ሩሽዲ (ፎቶ ፋይል፣ ኤፒ)

አጨቃጫቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ አንድ የጀርመን መጻሕፍት አሳታሚዎች እና ሻጮች ማሕበር የሚሰጠው የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኗል።

“ለሕይወት ባለው በጎ አመለካከት፣ በሥራው ለዓለም ባደረገው አስተዋጽ ኦሽልማቱን እንደሰጠው ማኅበሩ አስታውቋል።

በእ.አ.አ 1988 “ሳታኒክ ቨርስስ” “ሰይጣናዊ ጥቅሶች” በተሰኘው መጽሐፉ የሙስሊሙን ዓለም ያስቆጣው ሩሽዲ፣ በተለይ የኢራኑ አያቶላ በተገኘበት እንዲገደል አውጀውበት ነበር።

የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ዜግነት ደርቦ የያዘውና፣ በእንግሊዝ ሥር ትደዳደር በነበረችው ሕንድ እ.አ.አ በ1947 የተወለደው ሩሽዲ፣ ባለፈው ዓመት በኒው ዮርክ በአንድ የስነ ጽሁፍ ዝግጅት ላይ በመናገር ላይ ሳለ በተደጋጋሚ በጩቤ ተወግቶ የቀኝ ዓይኑን ሙሉ ለሙሉ ሲያጣ፣ የግራ ዓይኑም ተጎድቷል።

ጥቃቱን በተመለከተ በመጪው ሚያዚያ የሚወጣ አንድ መጽሃፍ እንዳለው ታውቋል።

በፍራንክፈርት የሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ሳልማን ሩሽዲ ባደረገው ንግግር፣ “ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በማንኛውም ሁኔታ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል” ሲል ጥሪ አድርጓል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG