በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሊባኖስ ውስጥ ዘገባ ላይ የነበረ የሮይተርስ ጋዜጠኛ ተገደለ


እኤአ ጥቅምት 13፣ 2023 በደቡብ ሊባኖስ ሲዘግብ የተገደለው የሮይተርስ ጋዜጠኛ ኢሳም አብደላህ (እኤአ፣ ሐምሌ 4፣ 2023 ሊባኖስ ውስጥ የተነሳው ፎቶ )
እኤአ ጥቅምት 13፣ 2023 በደቡብ ሊባኖስ ሲዘግብ የተገደለው የሮይተርስ ጋዜጠኛ ኢሳም አብደላህ (እኤአ፣ ሐምሌ 4፣ 2023 ሊባኖስ ውስጥ የተነሳው ፎቶ )

ደቡብ ሊባኖስ ውስጥ ሲዘግብ የነበረ የሮይተርስ ጋዜጠኛ ትናንት ዓርብ ሲገደል ሁለት የሮይተርስ ጋዜጠኞችና ሌሎች በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸውን የዜና ወኪሉ ሮይተርስ አስታውቋል፡፡

የሮይተርስ ቃል አቀባይ ትናንት ዓርብ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ “የቪዲዮ ፎቶግራፈራችን ኢሳም አብደላህ መገደሉን ስንሰማ እጅግ በጣም አዝነናል።” ብለዋል፡፡

አብደላህ በደቡባዊ ሊባኖስ የሮይተርስ ቡድን አባል ሲሆን በአድማው ወቅት የቀጥታ ስርጭት ዘገባውን ሲያቀርብ ነበር ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።

ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በመተባበር ፣ የኢሳምን ቤተሰብ እና የስራ ባልደረቦችን በመደገፍ ስለሁኔታው በአስቸኳይ ተጨማሪ መረጃዎች እንፈልጋለን። በዚህ አስከፊ ጊዜ ሀዘናችን ከቤተሰቦቹ ጋር ነው” ሲሉም ቃል አቀባዩ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የሮይተርስ ጋዜጠኞች ጣየር አል-ሱዳኒ እና ማህር ናዝህ የቆሰሉ በመሆናቸው ህክምና ይፈልጋሉ ሲሉም ቃል አቀባዩ አክለው ገልጸዋል።

የአልጀዚራ የዜና ማሰራጫ በበኩሉ ካርመን ጆክሃዳር እና ኤሊ ብራኪያ በተመሳሳይ ጊዜ መቁሰላቸውን አስታውቋል፡፡

ጉዳቱ ስለተፈጸመበት ሁኔታ ዝርዝር መረጃ አልተሰጠም፡፡

የእስራኤል ጦር ከሊባኖስ ጋር ባለው ድንበር አካባቢ ለተተኮሱበት ሮኬቶች እና ታጣቂዎች ጥቃት ምላሽ ሰጥቷል።

የሮይተርስ ጋዜጠኞች ከእነዚህ ጥቃቶች በአንዱ ተመትተዋል ተብሎ ይታመናል ሲሉ አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እና አልጀዚራ ዘግበዋል።

ይህ ስለመሆኑ ቪኦኤ ወዲያውኑ ማረጋገጥ አልቻለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG