በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በተመድ የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት መቀመጫዋን አጣች


የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ የአዳዲስ አባላትን የምርጫ ውጤት፣ ኒውዮርክ በሚገኘ የምክር ቤቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርበው ሲያነቡ። መስከረም 29/2016 ዓ.ም
የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ የአዳዲስ አባላትን የምርጫ ውጤት፣ ኒውዮርክ በሚገኘ የምክር ቤቱ ዋና መስሪያ ቤት ቀርበው ሲያነቡ። መስከረም 29/2016 ዓ.ም

ሩሲያ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2022 ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ በጠቅላላ ጉባኤ ከታገደች በኋላ በአወዛጋቢው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የነበራትን መቀመጫ ለማስመለስ ያደረገችው ጥረት ዛሬ ማክሰኞ ከሽፏል።

“የተባበሩት መንግሥታት አባል አገራት ለቁጥር የሚያታክቱ የጦር ወንጀሎችና የሰብአዊነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆነ መንግሥት በሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ውስጥ እንደማይገባ ለሩሲያ አመራር ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል” ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት የሂዩማን ራይትስ ዎች ዳይሬክተር ልዊስ ቻርቦኔው ተናግረዋል፡፡

በምስጢር በተሰጠ ድምጽ አልባኒያ፣ ቡልጋሪያ እና ሩሲያ በምስራቅ አውሮፓ ክልል ለተመደቡ ሁለት ክፍት መቀመጫዎች ተወዳድረዋል፡፡

ከሚያስፈልገው 97 አጠቃላይ ድምጽ ውስጥ ሞስኮ ያገኘችው 83 ሲሆን፣ ቡልጋሪያ 160 አልባኒያ ደግሞ 123 ድምጾችን አግኝተዋል፡፡

ከድምጽ አሰጣጡ አስቀድሞ የመብት ተሟጋቾች በዩክሬን ከተፈፀሙት አሰቃቂ ድርጊቶች በተጨማሪ ክሬምሊን ወረራው ከተጀመረ ጀምሮ በአገር ውስጥ መብቶች እና ነጻነቶች ላይ የተጣሉ ገደቦችን በማጠናከሯ ወደ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት መመለስ አይገባትም ሲሉ አስጠንቅቀው እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ጠቅላላ ጉባኤው መቀመጫውን ጄኔቫ ላይ ላደረገውና 47 አባላትን ለያዘው የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ለሶስት ዓመታት ክፍት የሆኑ 15 መቀመጫዎች መሙላት እንደነበረበት ተነግሯል፡፡

አሁን የምክር ቤቱ አባል የሆነችው ቻይና፣ 'clean slate' በመባል በሚታወቀውና በተመደቡ መቀመጫዎች ልክ እኩል ተፎካካሪ እጩዎችን ያቀረቡ አገሮች በሚወዳደሩበት በመቅረብ ለሁለተኛ ጊዜ አሸንፋለች፡፡

በእስያ ክልል ከተመደቡ ቡድኖች አራቱን መቀመጫዎችን ለመሙላት የቀረቡት ቻይና፣ጃፓን፣ ኩዌት እና ኢንዶኔዢያ በመሆቸው የሚፈለገውን አብላጫ ድምጽ በቀላሉ የማግኘት እድላቸውን ከፍ አድርጎታል፡፡

ይህ ሆኖም ኢንዶኔዢያ 186፣ ኩዌት 183 እና ጃፓን 175 ሲያገኙ ቻይና 154 ድምፅ በማግኘት በውድድሩ የመጨረሻ ሆናለች።

በተባበሩት መንግሥታት የሂዩማን ራይትስ ዎች ዳይሬክተር ልዊስ ቻርቦኔው “ቻይና በእስያ ምድብ የመጨረሻ ደረጃ ላይ መቀመጧ የሚያሳየው በእስያው ምድብ ውድድር ቢኖር ኖሮ ትሸነፍ ነበር" ማለት ነው ብለዋል ።

"መሆን የነበረበት ያ ነው። ይህ በተመድ የምርጫ ውድድር ምድቦች ወሳኝ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑን ያጎላል።” ሲሉ ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ አባላትን ለሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት ሲመርጥ የአልባኒያ ልዑካን ቡድን አባላት በኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት መስከረም 29፣ 2016 ዓ.ም
የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ አዲስ አባላትን ለሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባልነት ሲመርጥ የአልባኒያ ልዑካን ቡድን አባላት በኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት መስከረም 29፣ 2016 ዓ.ም

አገራት የመረጧቸው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አገሮች በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ “የሰብአዊ መብቶችን በማስተዋወቅ እና በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛውን ደረጃ እንዲያስከብሩ” ይጠበቅባቸዋል።

የመብት ተሟጋቾች ደካማ የመብት አጠባበቅ ታሪክ ያላቸው ሀገራት በምክር ቤቱ ውስጥ ያላቸውን አቋም ለጥቃት መሸፈኛ አድርገው ይጠቀሙበታል ሲሉ ያስጠነቅቃሉ።

የቻይና የሰብአዊ መብት ጥሰት በሚገባ ይታወቃል። በአገር ውስጥ ቤጂኒግ የመንግሥት ተችዎችና የሰብአዊ መብት ተከለካዮችን በዘፈቀደ ታስራለች፡፡ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ የኡጉር ሙስሊሞችን በዢንጂያንግ ግዛት በሚገኙ “የእምነት ማስቀየሪያ የተሃድሶ ትምህር ቤት ካምፖች” (reeducation camps”) ውስጥ አስሯለች። በሆንግ ኮንግ እና በቲቤት ውስጥም እንዲሁ ነፃነቶች በኃይል ታፍነዋል።

በላቲን አሜሪካ እና ካሪቢያን ምድብ ብራዚል፣ ኩባ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ እና ፔሩ ለሶስት መቀመጫዎች ተወዳድረዋል። መብት ደፍቂ ናት የተባለችው ኩባ 146 ድምፅ በማግኘት ትልቁን ድምፅ አግኝታለች። ብራዚል 144 ስታገኝ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ በ137 ድምጽ አሸንፋለች። በውድድሩ ዝቅተኛውን 108 ያገኘችው ፔሩ አልተሳካላትም፡፡

በአፍሪካው ምድብ ተፎካካሪ ላልነበረባቸው አራት ባዶ ቦታዎች የቀረቡት አራቱ አገራት ብሩንዲ፣ ጋና፣ አይሮቪሪ ኮስት እና ማላዊ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡

ፈረንሳይ እና ኔዘርላንድስ በምእራብ አውሮፓ እና በሌሎች ምድቦች የሚገኙትን ሁለት መቀመጫዎች በመሙላት የሚያስፈልገውን የአብላጫ ድምጽ አግኝተዋል፡፡

የጠቅላላ ጉባኤው አባላት
የጠቅላላ ጉባኤው አባላት

የሂዩማንዋቹ ዳይሬክተር ቻርቦኔው በብዙ ምድቦች ተፎካካሪዎች ባለመቅረባቸው ቻይና፣ ብሩንዲ እና ኩባ አሁን በምክር ቤት ውስጥ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

“ያስመዘገቡት እጅግ መጥፎ የሆነው የመብት አያያዝ ታሪካቸው ውድቅ ሊያደጋቸው ይገባ ነበር” ያሉት ዳይሬክተሩ

"ከዚህ ቀደም ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራት በተሳካ ሁኔታ እንዳደረጉት ሁሉ የእነዚህን ሶስት በዳዮች እና አጋሮቻቸውን ፀረ-ሰብአዊ መብት አጀንዳዎች ለመመከት መስራት አለባቸው።" ብለዋል፡፡

አሸናፊዎቹ የሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የአባልነት ጊዚያቸውን እኤአ ጥር 2024 ይጀምራሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG