በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራዊያን ስደተኞች ግጭትን ተከትሎ ኔታኒያሁ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ከእስራኤል ለማስወጣት አዘዙ


በእስራኤል ቴል አቪቭ የኤርትራዊያን ስደተኞች ግጭት
በእስራኤል ቴል አቪቭ የኤርትራዊያን ስደተኞች ግጭት

በትላንትናው ዕለት በቴል አቪቭ ጎዳናዎች ላይ በኤርትራዊያን ስደተኞች መካከል የተፈጠረውን አስከፊ ግጭት ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ደም በተቃባው ግጭት ላይ የተሳተፉት ስደተኞች በሙሉ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ እንደሚሹ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ሁሉም አፍሪካዊያን ስደተኞች ከእስራኤል እንዲወጡ ለሚያዝ እቅድ ፍቃድ መስጠታቸውንም ገልጸዋል።

ትላንት ቅዳሜ የፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደርን በሚቃወሙ እና በሚደግፉ ኤርትራዊያን መካከል ግጭቱ ተነስቷል። ተቃውሞውና ግጭቱ በእስራኤል ኤርትራ ኤምባሲ ፊት ለፊት ነው የተካሄደው። የእስራኤል የአደጋ አገልግሎት ተቋም 114 ሰዎች በግጭቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።

የእስራኤል ፖሊሶች የግጭቱን ተሳታፊዎች ለመበተን የፕላስቲክ ቦምቦችን የተጠቀሙ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ በፖሊሶቹ ላይ ድንጋይ ወርውረዋል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ፖሊስ ተቃዋሚዎቹ ላይ እሳት መርጨቱን የዘገበ ሲሆን በአጸፋው 27 ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲል አስታውቋል። በተያያዘ ሮይተርስ እጃቸው እና ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች በህጻናት መጫወቻ ሜዳዎች ሲደበቁ መመልከቱን ዘግቧል።

በእስራኤል 20,000 ኤርትራዊያን ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹም በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው የመጡ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG