በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብጽ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ላይ ድርድራቸውን ቀጥለዋል


ፋይል ፎቶ (ኤፒ)
ፋይል ፎቶ (ኤፒ)

ግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን፣ ተቋርጦ የነበረውንና ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው የህዳሴ ግድብ ላይ የሚያደርጉትን ድርድር ዛሬ ካይሮ ላይ እንደገና መቀጠላቸውን ባለስልጣናትን ጠቅሶ አሶስዬትድ ፕረስ ዘግቧል።

ድርድሩ የቀጠለው፣ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደል ፋታህ አል ሲሲ፣ በኢትዮጵያ እየተገነባ ባለው የህዳሴ ግድብ ጉዳይ፣ በአራት ወራት ውስጥ ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ባለፈው ወር ማስታወቃቸውን ተከትሎ ነው።

4.6 ቢሊዮን ዶላር የሚፈጀው ግድብ ፍላጎቷን ከግምት ውስጥ የማያስገባ ከሆነ፣ የናይልን ወንዝ ለግብርና እና 100 ሚሊዮን ለሚሆን ሕዝቧ የውሃ ፍጆታ የምትጠቀመው ግብጽ ትልቅ ስጋት እንደሚሆንባት ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

የግብጽ የመስኖ ሚኒስትር ሃኒ ሰዊላም ንግግሩ መጀመሩን አብስረው፣ የግድቡን አጠቃቀም እና የውሃ አሞላል በተመለከተ ግብጽ ሕጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ እንደምትሻ አስታውቀዋል። በርካታ “ቴክኒካዊ እና ሕጋዊ መፍትሄዎች” አለ ያሉት ሚኒስትሩ፣ በተናገሩት ላይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ስምምነት ከመፈጸሙ በፊት ኢትዮጵያ ግድቡን በመሙላቷ፣ በካይሮ እና በአዲስ አበባ መካከል ውጥረት ሰፍኖ ቆይቷል።

ለተከታታይ ዓመታት ድርቅ የሚከሰት ከሆነ፣ ኢትዮጵያ ምን ያህል ውሃ ትለቃለች፣ እንዲሁም ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ጭቅጭቆችን ሶስቱ ሃገራት እንዴት መፍትሄ ሊሰጡት ይችላሉ የሚሉት ካለተመለሱት ጥያቂዎች ውስጥ ይገኙበታል።

ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነትን እንደማትቀበል በፕሮጀክቱ መጨረሻ ማስታወቋን የሮይተርስ ዘገባ አስታውሷል።

አብዛኛው የሀገሪቱ ሕዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ባለመሆኑ፣ ግድቡ አስፈላጊ እንደሆነ ኢትዮጵያ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡

ሱዳን በበኩሏ፣ ጎርፍ እንዳይከሰት ለማድረግ እና ኃይል አመንጪ ግድቦቿን ለመከላከል በሚል፣ በግድቡ አጠቃቀም ላይ ኢትዮጵያ መረጃዎችን እንድታጋራ እና እንድትተባበር ትጠይቃለች፡፡ የህዳሴው ግድብ የሚገኘው ከሱዳን ድንበር 10 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ነው።

ጥቁር ዓባይ እና ነጭ ዓባይ ካርቱም ላይ ተገናኝተው ውሃው በግብጽ አድርጎ ሜዲትሬንያን ባህርን ይቀላቀላል። ከውሃው 85 በመቶ የሚሆነው የሚነሳው ከኢትዮጵያ ነው።

///

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG