በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወልቂጤ ውስጥ ከቤት ያለመውጣት አድማ መደረጉን ነዋሪዎች ተናገሩ


ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋራ ኾነው ወልቂጤ ከተማ ውስጥ ዛሬ ጠዋት ከጉራጌ ዞን ወረዳዎች እና ከተሞች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋራ ሲወያዩ። ፎቶ ከደቡብ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተወሰደ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋራ ኾነው ወልቂጤ ከተማ ውስጥ ዛሬ ጠዋት ከጉራጌ ዞን ወረዳዎች እና ከተሞች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋራ ሲወያዩ። ፎቶ ከደቡብ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተወሰደ።

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለአምስተኛ ጊዜ ከቤት ያለመውጣት አድማ መደረጉን ቪኦኤ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪች ተናገሩ።

አድማው የተደረገው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከዞኑ ወረዳዎች እና ከተሞች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋራ ለመነጋገር ዛሬ ወልቂጤ ከተማ በተገኙበት ዕለት መሆኑን ነዋሪዎቹ ጨምረው ገልፀዋል።

በዞኑ በክልልነት ከመደራጀትና፣ ከውሃ እጥረት ጋራ በተያያይዘ በቅርቡ ተደጋጋሚ ተቃውሞች ሲካሄዱ የቆዩ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከዞኑ ወረዳዎች እና ከተሞች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋራ ለመነጋገር ዛሬ ወልቂጤ እንደሚገቡ አስቀድሞ መታወቁ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁን አንድ የከተማው ነዋሪ በስልክ በሰጡን አስተያየት ከቤት ውስጥ ያለመውጣት አድማው ተደረገ የተባለበትን ምክኒያት ሲያስረዱ ፤ "ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደዚህ መመጣታቸው ከታወቀ በኃላ ማኅበረሰቡ እሳቸውን ወጥቶ ለመቀበል ተዘጋጅቶ ነበረ። ከመንግሥት አካለትም ትዕዛዝ ተላልፎ ነበር።" ብለዋል።

አያይዘውም "ጠቅላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ለመያየት የተጠሩት ስለከተማው ስለዞኑ ምንም ከማያውቁ ግለሰቦች መሆኑ በመሰማቱ የከተማው ነዋሪ በጣም አኮረፈ፤ በጣም ተቆጣ። ለምን የማኅበረሰቡና የከተማችን ችግር የምናውቀው እኛ ነን። ያ ሳይሆን እኛን አይወክሉንም በሚል ሁሉም አኩርፎ ቤቱ ቁጭ አለ ማለት ነው።” ብለዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር ለመወያየት ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋራ ኾነው ዛሬ ጠዋት ጉራጌ ዞን መግባታቸውን በጽሕፈት ቤታቸው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ሰፍሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት መሳተፋቸውን ተገለፁት አቶ ሃቢብ ከድር ለውይይቱ ከአንድ ወረዳ 40 ሰዎ መወከሉን ገልፀዋል። "ከቀቤና ወረዳም 40 ሰዎች ከወጣቱም ከሽማግሌዎች ተወጣጥቶ ውይይቱ ላይ ተሳትፏል።

በውይይቱም በቀቤና በኩል የልዩ ወረዳ ጥያቄ ተነስቷል። ክልል በተመለከተም በአንድነት መደራጀት እንደሚጠቅም ተነስቷል። ከሌሎች የጉራጌ ወረዳዎችም ከክልል ጋር ተያይዞ ከልማት ጋር የተወከሉም ጥያቄ አንስተዋል።" ብለዋል።።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽም በአሁኑ ወቅት በተናጥል ክልል የሚደረግበት ሁኔታ እንደሌለና ሕዝቡ በአንድነቱ ፀንቶ መኖር እንደሚገባው መናገራቸውን አቶ ሃቢብ ጠቁመዋል።

ሰባት የኢዜማ ፓርቲ ፤ 12 ጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ (ጎጎት) ፓርቲ አባላት እንዲሁም ሌሎች ሲቪሎችን ጨምሮ ከ45 በላይ ሰዎች ከአዲስ አበባ ጭምር በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው በቡታጅራ ከተማ መታሰራቸውን የፓርቲዎቹ አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ መናገራቸው አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG