በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩጋንዳ በአዲስ ዓመት በዓል አከባበር ላይ ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ


ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በአንድ የገበያ ሥፍራ (ሞል) አቅራቢያ የነበረን የርችት ተኩስ ለመመልከት የተሰባሰቡት ሰዎች ጀንዋሪ 1/2023 ዓ.ም
ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በአንድ የገበያ ሥፍራ (ሞል) አቅራቢያ የነበረን የርችት ተኩስ ለመመልከት የተሰባሰቡት ሰዎች ጀንዋሪ 1/2023 ዓ.ም

በዩጋንዳ አዲስ ዓመት አከባበር ላይ በተፈጠረ መጨናነቅ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ከሟቾቹ አብዛኞቹ ከ10 እስከ 20 ዓመት እድሜ ያላቸው ናቸው ተብሏል።

በመዲናዋ ካምፓላ በአንድ የገበያ ሥፍራ (ሞል) አቅራቢያ የነበረን የርችት ተኩስ ለመመልከት የተሰባሰቡት ሰዎች ሲጋፉ በተፈጠረ መረጋገጥ 5 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ አራቱ ደግሞ ወደ ሆስፒታል በመወሰድ ላይ ሳሉ ህይወታቸው አልፏል ሲል ኤ.ኤፍ.ፒ ዘግቧል። በርካታ ሰዎችም ተጎድተዋል።

ከሦስት ዓመት መቋረጥ በኋላ አዲሱን ዓመት በፌስታ ለመቀበል የተሰባሰቡት እድምተኞች ከፍ ካለ ቦታ ርችቱን ከተመለከቱ በኋላ ወደታች ሲወርዱ በተፈጠረ ግፍያ አደጋው ሊፈጠር ችሏል።

XS
SM
MD
LG