በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሚያ ቀውስ የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት መጠኑ እንዲጨርም አድርጎታል - ተመድ


keተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) ገፅ ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ ካወታው ሪፑት ላይ ከስክሪን ቅጂ የተወሰደ/ በነች የሚታየው መንቀሳቀስና እርዳታ ማድረስ የሚቻልባቸው/ ፈዛዛ ቀለም ያራፈባቸው ቦታዎች በከፊል መድረስ የሚቻልባቸው ቦታዎች ሲሆኑ ደማቆቹ ደግሞ ጭርሱኑ ምንም መድረስ የማይቻልባቸው ቦታዎች ናቸው።
keተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) ገፅ ላይ ኢትዮጵያን በተመለከተ ካወታው ሪፑት ላይ ከስክሪን ቅጂ የተወሰደ/ በነች የሚታየው መንቀሳቀስና እርዳታ ማድረስ የሚቻልባቸው/ ፈዛዛ ቀለም ያራፈባቸው ቦታዎች በከፊል መድረስ የሚቻልባቸው ቦታዎች ሲሆኑ ደማቆቹ ደግሞ ጭርሱኑ ምንም መድረስ የማይቻልባቸው ቦታዎች ናቸው።

በኦሮሚያ ክልል የሚታዩት የተለያዩ ቀውሶች የፈጠሩት ጫና የሰብዓዊ እርዳታ ፍላጎት መጠኑን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ማድረጉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ዩኤን ኦቻ) ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

በምዕራብ ኦሮሚያ፣ ወለጋ ከተማ የሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ዜጎችን እያፈናቀለ፣ መተዳደሪያንና መሰረተ ልማቶችን እያወደመ መሆኑንም ገልጿል።

“አካባቢው ተደራሽ ባለመሆኑ የአዲስ ተፈናቃዮች ቁጥር አልተረጋገጠም” ያለው ኦቻ፣ በአካባቢው በነበሩት ተፈናቃዮች ላይ ቁጥር ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እንደሚያመጣ አመልክቷል።

በምዕራብ ወለጋ ዞን ከ106 ሺህ በላይና በሆኖ ጉድሩ ወለጋ 116ሺህ ተፈናቃዮች እንዳሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ማረጋገጣቸውን የጠቀሰው ኦቻ፣ የክልሉ መንግሥት እየጨመረ የመጣውን የተፈናቃዮች ፍሰት የሚመጥን ተጨማሪ የተፈናቃዮች ቦታ በማቋቋም ላይ መሆኑን ገልጿል።

"ፍላጎቱ ምላሽ ለመስጠት ከሚደረገው ጥረት በላይ ናቸው" ያለው ኦቻ ፤ በምዕራብ ወለጋ ዞን እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው 19ሺህ አባወራዎች መካከል 1ሺህ 100 የሚሆኑት፣ እንዲሁም በምስራቅ ወለጋ ዞን ድጋፍ ከሚሹ 30ሺህ አባወራዎች መካከል 9ሺህ 337 የሚሆኑት ብቻ ከመጠለያና ምግብ ውጪ ያሉ ድጋፎች ማግኘታቸውን አመልክቷል። በተመሳሳይ በጉጂና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች የሚስተዋሉ ግጭቶች የእርዳታ ፍሰቱን እያደናቀፉ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

የኦቻ መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በተለይ በድርቅ በተጎዱ ዞኖች የምግብ እጥረት አሳሳቢነት እየጨምረ መሄዱን አስታውቋል። በቅርቡ በተደረገ ጥናት ምርመራ ከተደረገላቸው ከ563ሺህ ህፃናት መካከል 1.96 ከመቶ የሚሆኑት በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትና 18 ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ በመካከለኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል። በጉጂ ዞን የተገኘው ውጤት ደግሞ የበለጠ አሳሳቢ መሆኑን የገለፀው ኦቻ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት እጥረትና የአጋር ድርጅቶች ቁጥር ዝቅተኛ መሆን ፈታኝ ሆኖ መቀጠሉን ጠቅሷል።

ከኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ ድርቅ በሶማሌ ክልል አፍደር፣ ዳዋ፣ ሊባን እና ሸበሌ ዞኖች መተዳደሪያዎችን ማውደሙን መቀጠሉን ኦቻ አስታውቋል። "በተለይ በአፍደር ዞን ከ230ሺህ የማያንሱ የቀንድ ከብቶች፣ 125ሺህ 460 የሚሆኑት በምግብ እጦት እና 104ሺህ 540 የሚሆኑት በበሽታ ማለቃቸው አሳሳቢ ነው" ሲልም አመልክቷል።

በአጠቃላይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጠን እያሻቀበ ሲሆን በመስከረም ወር በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጎድተው ወደ ጤና ማዕከል የገቡ ህፃናት ቁጥር 10ሺህ 743 ደርሷል።

በተመሳሳይ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፣ በሲዳማና በደቡብ ምዕራብ ክልሎች ድርቅ ያከተለው የምግብ እጥረት እየተባባሰ የሄደ ሲሆን እርዳታ ከሚያስፈልገው 70 ከመቶ ለሚሆነው ምላሽ መሰጠቱን የኦቻ መግለጫ አክሎ ገልጿል።

የበጋው ዝናብ በነዚህ አካባቢዎች የመሻሻል ምልክት በማሳየቱ የውሃ እና የግጦች አቅርቦት ሊጨምር ይችላል ያለው ኦቻ ይህ ምናልባት በመጪዎቹ ወራት የእንስሳትን ሁኔታ እና የምግብ አቅርቦትን ሊያሻሽል ይችላል የሚል ተስፋ አመላክቷል።

XS
SM
MD
LG