ዩናይትድ ስቴትስ ታሊባን ፓኪስታን ውስጥ የሽብረተኛ ቡድኖች በመዋጋት በኩል ተገቢውን ስራ እየሰሩ አይደለም በሚል ስጋቷን እየገለጸች ባለችበት በአሁኑ ሰዓት ቅዳሜ ዕለት አፍጋኒስታን ውስጥ ለተገደሉት ፓኪስታናዊ ዲፕሎማት የግድያ ሙከራ ሃላፊነቱን እንደሚወስድ እስላማዊ መንግስት በመባል የሚታወቀው የሽብር ቡድን ገለጸ።
የአፍጋኒስታን ባለስልጣናት የፓኪስታኑ ቆንስላ ኡበይድ-ኡር-ረህማን ኒዛማኒ ካቡል በሚገኘው ኤምባሲ ቅጽር ግቢ ውስጥ የተለመደ የከሰዓት የእግር ጉዟቸውን ሲያደርጉ ሳሉ በአቅራቢያ ካለ ህንጻ ላይ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስታውቀዋል።
ይህን ተከትሎም እሳቸው ምንም ሳይደርስባቸው ቢያመልጡም የደህነነት ተባቂያቸው ግን ደረቱን እና እግሮቹን በጥይት መመታቱ ታውቋል።
ፓኪስታን ጥቃቱን ያወገዘች ሲሆን ታሊባን አጥቂዎቹን ለህግ እንዲያቀርብ እና በአፍጋኒስታን ለሚገኘው ልዑኳ የሚያደርገውን የደህንነት ጥበቃ እንዲያጠናክር ጠይቃለች።