በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዲሞክራቶች ሕግ መወሰኛ ም/ቤቱን እንደተቆጣጠሩ ይቆያሉ


ሴናተር ካትሪን ኮርቴዝ ማስቶ (በስተገራ) ከኔቫዳው አገረ-ገዢ ስቲቭ ሲሶላክ ጋር ባለፈው ማክሰኞ የምርጫ ምሽት ስብሰባ ላይ ይታያሉ (ኖቬምበር 8፣ 2022)
ሴናተር ካትሪን ኮርቴዝ ማስቶ (በስተገራ) ከኔቫዳው አገረ-ገዢ ስቲቭ ሲሶላክ ጋር ባለፈው ማክሰኞ የምርጫ ምሽት ስብሰባ ላይ ይታያሉ (ኖቬምበር 8፣ 2022)

በአሜሪካ የፕሬዝደንታዊ አጋማሽ ዘመን የምርጫ ፉክክር የዲሞክራቲክ ፓርቲ የሕግ መወሰኛ ም/ቤቱን መቆጣጠሩ ታውቋል።

ትናንት ቅዳሜ ማምሻውን በኔቫዳ ግዛት የዲሞክራቲክ ፓርቲ ወኪሏ ሴናተር ካትሪን ኮርቴዝ ማስቶ ድል ሲቀናቸው ፓርቲው 50 መቀመጫ በሕግ መወሰኛ ም/ቤቱ ማግኘቱን አረጋግጧል። ሪፐብሊካኖቹ 49 አግኝተዋል።

“ሰዎች በብዛት ወጥተው በመምረጣቸው አልተገረምኩም፣ መጣም ደስተኛ ነኝ” ብለዋል ለስብሰባ ካምቦዲያ የሚገኙት ዲሞክራቲኩ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዜናውን እንደሰሙ።

በኔቫዳና በአሪዞና ድል የቀናቸው ዲሞክራቶች 50 መቀመጫ እንደያዙ አሶስዬትድ ፕሬስ ቅዳሜ ማምሻውን ዜናውን አብስሯል።

አሁን ያልለየለት የጆርጂያው ምርጫ ሲሆን፣ ሪፐብሊካኑ ቢያሸንፉትና 50 እኩል መቀመጫ ቢኖራቸው እንኳ፣ ዲሞክራቲኳ ም/ፕሬዝደንት ካመላ ሃሪስ የሕግ መወሰኛው ም/ቤት ፕሬዝደንትም በመሆናቸው አንድ ገላግሌ ድምጽ ስለሚኖራቸው ም/ቤቱን ይቆጣጠራሉ።

XS
SM
MD
LG