በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዩናይትድ ስቴትስ የሚነሱ የተመላሽ ስደተኛ በረራዎችን ለመቀበል ኩባ ተስማማች


ምስሉ በሜክሲኮ ድንበር በኩል ተሻግረው እጃቸውን የሰጡ የኩባ ሴቶችን ያሳያል ።
ምስሉ በሜክሲኮ ድንበር በኩል ተሻግረው እጃቸውን የሰጡ የኩባ ሴቶችን ያሳያል ።

የኮቪድ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ኩባ ፣በዩናይትድ ስቴትስ እና ሜክሲኮ ድንበር መካከል ተይዘው ወደ ሀገራቸው ተመላሽ የሚደረጉ ስደተኞችን የጫኑ በረራዎችን ለመቀበል መስማማቷን ሶስት ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ ዘግቧል።ይህ እርምጃ ቁጥሩ እያሸቀበ የመጣውን የኩባ ድንበር ተሻጋሪዎችን ለመቆጣጠር አዲስ እና የተመጠነ ጉልበት ለዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት እንደሚሰጥ ተነግሯል።

የዩናይትድ ስቴትስ የስደት እና የጉምሩክ ባለስልጣን በምህጻሩ አይስ የቅድመ ማጣሪያ ደረጃዎችን ያላለፉ በርካታ ኩባዊያንን በቁጥጥር ስር እንዳደረገ ስማቸውን የሸሸጉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።የስደተኞቹ ቁጥር አውሮፕላን መሙላት ሲችል፣ ወደ ሀቫና እንደሚላኩም ተሰምቷል።

ሌላ ሶስተኛ የመረጃ ምንጭ አሁንም ድረስ የምልሰት በረራዎችን በተመለከተ በሀገራቱ መካከል መደበኛ ስምምነት ባፎኖርም፣ ኩባ አልፎ አልፊ በግዳጅ ተመላሽ ዜጎቿን ለመቀበል ተስማምታለች። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፣ ዋይት ኃውስ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ የስደት እና የጉምሩክ ባለስልጣን እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጡት ምላሽ እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG