በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ለጦሯ የክተት ጥሪ አደረገች


Eritrean soldiers march during the country's Independence Day in Asmara May 24, 2007.
Eritrean soldiers march during the country's Independence Day in Asmara May 24, 2007.

ኤርትራ ለጦሯ የክተት ጥሪ ማድረጓንና የኢትዮጵያን መንግስት ከህወሃት ጋር እያደረገ ላለው ጦርነት ለመርዳት ልታንቀሳቅስ ይመስላል ሲሉ መንግስታት በመግለጽ ላይ መሆናቸውን የኤ.ኤፍ.ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የክተት ጥሪውን ተከትሎ፣ ዜጎቻቸው በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የእንግሊዝና የካናዳ መንግስታት ባወጡት የጉዞ ማስጠንቀቂያ አስታውቀዋል።

“የሰሜን ኢትዮጵያውን ግጭት ተከትሎ በኤርትራ ያሉ የየአካባቢው ባለስልጣናት ለሃገሪቱ ጦር አባላት አጠቃላይ ጥሪ አድርገዋል” ሲል የካናዳ መንግስት አስታውቋል።

“በመላ ሃገሪቱ ተጨማሪ የህንነት እገዳዎች ካለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሊተገበሩ ይችላሉ” ሲል የካናዳ መንግስት ጨምሮ አስታውቋል።

የእንግሊዝ መንግስት የክተት ጥሪው ረቡዕ መደርጉን ገልጾ ዜጎች ተጨማሪ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል።

ህወሃት ባለፈው እሁድ በአፍሪካ ህብረት ለሚደረግ ድርድር ፈቃደኛ እንደሆነ ሲገልጽ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለህወሃት መግለጫ ቀጥተኛ መልስ ባይሰጥም፣ በሕብረቱ ለሚደረግ የሰላም ንግግር ዝግጁ እንደሆነ ቀደም ብሎ ሲገልጽ ቆይቷል።

ካለፈው መጋቢት ጀምሮ ለአምስት ወራት ጋብ ብሉ የነበረው ጦርነት ነሃሴ 17 2014 ሲያገረሽ፣ ገጭቱ በሰላማዊ መንገድ ይፈታል የሚለውን ተስፋ አደብዝዞታል።

XS
SM
MD
LG