በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍቃሪ-ዴሞክራሲያኑን ተቃውሞ ሰልፎች ለመቆጣጠር ሱዳን ወታደሮቿን አሰማራች


የሱዳን የተቃዋሚ ስልፈኞች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በተደጋጋሚ ታጋጭተዋል።
የሱዳን የተቃዋሚ ስልፈኞች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በተደጋጋሚ ታጋጭተዋል።

በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የተቆናጠጡትን ጄኔራል አብደል ፈታ አል ቡራሃንን ለማቃዋም ፣ የሱዳን አፍቃሪ-ዴሞክራሲ ቡድኖች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን ተከትሎ፣ በዛሬው ዕለት ፖሊሶች እና ወታደሮችን በብዛት በዋና ከተማዋ ካርቱም ተሰማርተዋል።

የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ፣ የጸጥታ ኃይሎች ካርቱምን ከአጎራባች የመኖሪያ ስፍራዎች ጋር የሚያገናኙትን የናይል ወንዝ የሚሻገሩ ድልድዮች ዘግተዋል።በዚህ ያልተበገሩ የሚመስሉት ፣ ተቃዎሚዎች በአንጻራዊነት ሰላማዊ ሆኖ የተከበረው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ቅዱስ በዓል-ኢድ አል አድሃ -ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ መጠናቀቁን ተከትሎ ጎዳናዎችን በብዛት በመውጣት ለማጥለቅለቅ አቅደዋል።

ተቃዋሚዎች ጄኔራል ቡርሃን ባለፈው ጥቅምት ወር ጀምረው በጉልበት ስልጣን መያዛቸውን ይቃዋማሉ። ከካርቱም 450 ኪሎሜትሮች ርቆ በሚገኘው የብሉ ናይል ግዛት ያለው ከባድ ውጊያ ትኩረት እንዲያገኝም ይሻሉ ።

የሱዳን ውስጥ የቅርብ ጊዜ መፈንቅለ መንግስት ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር የምታደርገውን ሽግግር አስተጓጉሎታል። ከሳምንት ሳምንት ተብሎ ሊገለጽ በሚችል ደረጃ የተደጋጋሚ ተቃዋሞ ሰልፍ ምክንያት ሆኗል። በአፍቃሪ -ዴሞክራሲ ሐኪሞች መረጃ መሰረት ፣የጸጥታ ኃይሎች ሰልፎቹን ለመቆጣጠር በወሰዷቸው የኃይል እርምጃዎች እስካሁን በትንሹ 114 ሰዎች ተገድለዋል።

በአውሮፓዊያኑ ሀምሌ 4 ፣ ቡራሃን ባልተጠበቀ መልኩ ለሲቪል መንግስት ምስረታ መንገድ እንደሚከፍቱ ይፋ አድርገዋል። የሀገሪቱ ዋነኛ የሲቪል ቡድኖች ስብስብ ግን፣ እቅዱን “ማታለያ” ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል። ተቃዋሚዎች የሀገሪቱ የጦር ኃይል መሪ ከስልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG