በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያው ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ ቃለ መሃላ ፈፀሙ


ግንቦት 7 / 2014 ዓ.ም. የሶማሊያ 10ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት የተመረጡት የ66 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ሐሰን ዛሬ ሰኔ 2/2014 ዓ.ም በዓለ ሲመታቸውን መቋድሾ ሶማሊያ ውስጥ በዓለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ።
ግንቦት 7 / 2014 ዓ.ም. የሶማሊያ 10ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት የተመረጡት የ66 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ሐሰን ዛሬ ሰኔ 2/2014 ዓ.ም በዓለ ሲመታቸውን መቋድሾ ሶማሊያ ውስጥ በዓለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ።

የሶማሊያ 10ኛ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ሐሰን ሼክ ሞሃሙድ ሥራቸውን ዛሬ በይፋ ጀመሩ።ዛሬ ሞቃዲሾ ላይ በተካሄደው የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ ሁለት የጎረቤት አገር ፕሬዚዳንቶች ሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮችና 100 ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ከአንድ ሺ በላይ እንግዶች ታድመዋል።

ግንቦት 7 / 2014 ዓ.ም. የተመረጡት የ66 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ሐሰን “የሶማልያን ክብር ለማስመለስ፣ ከዓለም ጋር መልካም ግንኙነት ለመመሥረትና በአገሪቱ ሰላምና እርቅ ለማውረድ” እንደሚተጉ ቃል ገብተዋል።

በየመካከሉ በብዙ ሆታና ጭብጨባዎች በታጀበው ንግግራቸው የተስፋፋውን የሰላምና ደኅንነት መጥፋት፣ ሙስናን፣ ድህነትን ለማስወገድ፣ እንዲሁም የፍትኅ ተሀድሶና የምጣኔ ሃብት ዕድገት ለማምጣት፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ አገሪቱ የተጋረጠባትን ሰብዓዊ ቀውስ ለማስወገድ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው ሶማልያ የአፍሪካን ቀንድ በተደጋጋሚ በሚያጠቃው ድርቅ የተነሳ ለከፍተኛ ረሀብ መጋለጧን ጠቁመው መንግሥታቸው በድርቁና በሌሎች የተፈጠሮ አደጋዎች ላይ የሚሠራ አካል እንደሚያቋቋም ገልፀዋል።

በሶማልያዊያን መካከል እርቅ እንዲወርድና አገሪቱ ወደ ተረጋጋ ህይወት እንድትመለስ እንደሚጥሩ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ሃሰን “አገራችን ከዓለምም ሆነ ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላምና ወዳጅነት ሳትመሠርት የምንፈልገው ህልም እውን ሊሆን አይችልም” ብለዋል።

በስነ ሥር ዓቱ ላይ ንግግር ያሰሙት ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ማሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ህዝቡ አዲሱን ፕሬዚዳንትና መጭውን አስተዳደር በመደገፍ እስከ ዛሬ የተከናወኑና የተጀመሩ ሥራዎችን ከግብ እንዲያደርስ ጠይቀዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቦሊና ከሌሎች ሃያ አገሮች ሞቃዲሾ የገቡ መልዕክተኞች ተገኝተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተናገሩት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬዚዳንቱ “ሶማልያን ለመንገባት ለሚያደርጉት ጥረት ሁሉ የኢትዮጵያ ድጋፍ እንደማይለያቸው ገልፀዋል።

አያይዘውም “በሶማልያ እስካሁን ያረጋገጥኩት ነገር ካሁን በኋላ በሶማልያ በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ ያለምርጫ የሚደረግ የሥልጣን ሽግግር አለመኖሩን ነው፤ ይህም ለዴሞክራሲ ጥሩ ምሳሌ ሊሆን ይችላል” በማለት አድናቆታቸውን ተናግረዋል።

ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ፋርማጆ ጋር መልካም ግንኙነት ያልነበራቸው የኬንያና የጅቡቲ ፕሬዚዳንቶችም ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG