በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩን ከሥራ አገዱ


ፋይል - የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሳኢድ ሙሴ አሊ ብራሰልስ በሚገኘው የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ህንፃ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር የካቲት 17/ 2020 ዓ.ም ለአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ጉባኤ በተገኙበት ወቅት
ፋይል - የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሳኢድ ሙሴ አሊ ብራሰልስ በሚገኘው የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ህንፃ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር የካቲት 17/ 2020 ዓ.ም ለአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ጉባኤ በተገኙበት ወቅት

የሶማሊያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴን ሮብሌ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዲሰይድ ሙሴን በሕገወጥ መንገድ ከሰል ወደ ኦማን እንዲላክ ፈቃድ ሰጥተዋል በሚል ከሥራ አግደዋቸዋል።

የሶማሊያ መንግስት የደን መመንጠርን ለመከላከል እንዲሁም ከከሰል ሽያጭ የሚገኘው ገንዘብ በአካባቢው የሚካሄዱ ግጭቶችን መደገፊያ እንዳይሆን ከአስር ዓመት በፊት ከሰልን ለውጪ ገበያ ማቅረብን አግዷል።

የአካባቢው ተንታኞች ግን "ለባለሥልጣኑ መታገድ እውነተኛው ምክንያት ከሰል እንዲላክ መፍቀዳችው አይደለም" ይላሉ።

እንደ ተንታኞቹ ከሆነ የመባረር ያህል የሚቆጠረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ መታገድ የሚጠበቅ እርምጃ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብሌ ራሳቸው በአዲሱ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃሙድ ሊተኩ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የ”ሶማሊያ የሕዝብ አጀንዳ” በመባል የሚታወቀው የምርምር ቡድን ምክትል ኃላፊ ኢሳክ ፋራን እንዳሉት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አብዲ ሰይድ ሙሴ ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ፎርማጆ ጋር ቅርበት እንዳላቸው እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ሮብሌ የሚላኩላቸውን ድብዳቤዎች ችላ ይላሉ። ከደብዳቤዎቹ አንዱ የአፍሪካ ህብረት ልዮ ልዑክ የነበሩት ፍራንሲስኮ ማዲዬራን ከሃገሪቱ ማስወጣትን የሚመለከተው ይገኝበታል።

ኢሳክ ፋራን እንዳሉት የከሰል ምርትን ወደ ውጪ ገበያ የመላክ በሶማሊያ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆን እና ሃገሪቱ እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር በ2012 ከተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ም/ቤት ጋር ባደረገችው ስምምነት መሰረት ከሰልን ለውጪ ገበያ ማዋል ታግዷል። የተ.መ.ድ. ተቆጣጣሪዎችም ጉዳዩን በንቃት የሚመለከቱት ጉዳይ እንደሆነ አክለዋል።

የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ የከሰል ምርቱ እንዲወጣ ፈቃድ የመስጠታቸው ጉዳይ እንቆቅልሽ ቢሆንም የሶማሊያ ባለስልጣናት በመንግስት ሽግግር ወቅት ያለውን አጋጣሚ በመጠቀም ከሕዝቡ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም የሚያስቀድም ተግባር ውስጥ እንዲሚሳተፉ ሞሃመድ ሼክ ኖር ለቪኦኤ የላከው ዘገባ ያመለክታል።

XS
SM
MD
LG