በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቆይታ፦ ከስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አማካሪ ቤርናር ላውራንዱ ጋር


የኢትዮጵያ ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከፍተኛ አማካሪ ቤርናር ላውራንዱ
የኢትዮጵያ ስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከፍተኛ አማካሪ ቤርናር ላውራንዱ

በአውሮፓዊያኑ 2030 ዓመተ ምህረት ለዜጎቿ 20 ሚሊየን አዳዲስ ስራዎቿን ለመፍጠር ያቀደቸው ኢትዮጵያ፣ ካለመችበት ለመድረስ የተለያዩ መርሀ-ግብሮች በመተግበር ትገኛለች።

ከእነዚህ መካከል በሳይንስ ፣ቴክኖሎጂ ፣ ምህንድስና እና ሂሳብ ትምህርቶች (STEM) በየዓመቱ የሚመረቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ለእንጀራ ያበቃል ብላ ተስፋ የጣለችበት በእንግሊዝኛ ምህጻሩ፣ FROG የተሰኘው መርሀ ግብር ይገኛል።

Freelancing, outsourcing and Gigs የሚሉ ቃላትን ያቀናጀው አሰራር ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ጥራት ያለው አገልግሎት በተሻለ ዋጋ ከሚፈልጉ ሀገራት ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ተቋማት ስራዎችን በተለያየ የውል ግንኙነት አማካኝነት ተረክበው የሚሰሩበት ዓይነት ነው።

ህንድን በመሰሉ ሀገራት የተለመደው አሰራር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ቢተገበር የዲጂታል ኢኮኖሚውን የማነቃቃት ፣ ለበርካቶች ስራ የመፍጠር አቅም አለው ብሎ ያመነው የኢትዮጵያ የስራ ዕድል ኮሚሽን ተዛማች ስራዎችን ከጀመረ ሰነባብቷል።

ስለ መርሐ-ግብሩ ለማወቅ እና ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሀብታሙ ስዩም ወደ አቶ ቤርናር ላውራንዱ ደውሏል። አቶ ቤርናር ከ10 ዓመት ለተሻገረ ጊዜ በተለያዩ የዓለም ሀገራት የዲጂታል ስርዓትን በተመለከተ አማካሪ ሆነው ሰርተዋል። በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን በከፍተኛ አማካሪነት እያገለገሉ ይገኛሉ።

አስቀድመው ኢትዮጵያ ከሌሎች ዘርፎች በተለየ ዲጂታል ኢኮኖሚ ላይ ማተኮር ለምን እንዳስፈለጋት ያስረዳሉ፦

ቆይታ፦ ከስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን አማካሪ ቤርናር ላውራንዱ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:08 0:00


XS
SM
MD
LG