በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስኬታማዎ ትውልደ-ኢትዮጵያዊት ስደተኛ ጣልያን ውስጥ ሞተው ተገኙ


አጊቱ ጉደታ በሰሜን ጣልያን በሚገኝ የከብት ርባታ ጣቢያቸው።
አጊቱ ጉደታ በሰሜን ጣልያን በሚገኝ የከብት ርባታ ጣቢያቸው።

በጣልያን ሰሜን ትሬንቲኖ ግዛት በከፈቱት ስኬታማ የእንስሳት እርባታ ጣቢያ እና የአይብ መደብር ትኩረትን ስበው የነበሩት ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ አጊቱ ጉደታ በቤታቸው ሞተው መገኘታቸው ተሰምቷል።

የጣልያን ፖሊስን ዋቢ ያደረጉ መገናኛ ብዙሀን አጊቱ በሰው እጅ ህይወታቸው ሳይጠፋ እንዳልቀረ አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን እየተከታተለው እና የምርመራ ውጤቱን ከፖሊስ እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል።

ሀብታሙ ስዩም ዝርዝር ዘገባ አለው።

XS
SM
MD
LG