አትሌቲክስ፦
ኢትዮጵያዊው ሹራ ኪጣታ በትናንትናው ዕለት በተደረገው የለንደን ማራቶን ባለ ድል ሆኗል። ሌላኛው የሀገሩ ልጅ ቀነኒሳ በቀለ በውድድሩ እንደማይሳተፍ በዋዜማው ማስታወቁን ተከትሎ የዚህ ውድድር አሸናፊ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀው ኬንያዊው የተከታታይ ድሎች ባለቤት ኤልዩድ ኬፕቹጌ ነበር።
ሆኖም የ24 ዓመቱ ሹራ ቂጣታ የውድደሩ ግርምት ሆኗል̀። 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ኬንያዊውን ቪንሰንት ኪፕቹምባን አስከትሎ አሸንፈዋል። የሀገሩ ልጆች የሆኑት ሲሳይ ለማ ፣ ሞስነት ገረመው ፣ሙሌ ዋሲሁን እና ታምራት ቶላ ከሶስተኛ እስከ ስድስተኛ ደረጃ ያለውን ስፍራ በመያዝ ተከተለው ገብተዋል።
የለንደን ቀዝቃዛ አየር ሁኔታ ውድድሩን ፈታኝ እንዳደረገው ተጠቁሟል።ከ2013 የጎረጎሳዊያን ዘመን ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳያሸንፍ የቀረው የ35 ዓመቱ ኤልዩድ ኪፕቹጌ በቅዝቃዜው ምክንያት ጆሮው መደፈኑን የኃላ ኃላ ደግሞ እንዳያንቀሳቀስ ወደ አገደው ህመም ስሜት ማደጉን በምክንያትነት አቅርቧል።
የዛሬ ሁለት ዓመት በተደረገው የለንደን ኦሎምፒክ ላይ ሁለተኛ ወጥቶ የነበረው ሹራ ቂጠታ በበኩሉ ለአሁኑ ድሉ -በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ በመጨረሻው ሰዓት ያስታወቀውን ቀነኒሳ በቀለን አመሰግኗል።
"ቀነኒሳ ለዚህ ውድድር ሲያግዘኝ ነበር። እንዴት መሮጥ እንዳለብኝም መክሮኛል" ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።
ከተሳተፋባቸው 13 ማራቶኖች 12ቱን በድል ያጠናቀቀው ኪፕቾጌ በበኩሉ መሸነፉን በጸጋ መቀበሉን በቲዊተር ገጹ አስታውቆ -ወደ ውድድሩ ግን እንደሚመለስ አስታውቋል።
በዚሁ ዕለት ቀደም ብሎ በተደረገው የሴቶች ማራቶን ውድድር ኬንያዊቷ ብሪጊድ ኮስጌ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አሸንፋለች።አሜሪካዊቷ ሳራ ሀል ሁለተኛ ኬንያዊቷ ሳራ ቺፕንጌትች ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ተቆናጠዋል።
የዘንድሮው የለንደን ማራቶን ሊከናወን ቀጠሮ የተያዘለት በሚያዚያ ወር ላይ ነበር። ኮቪድ 19 ሁኔታዎችን በመቀየሩ ወደ ጎረጎሳዊያኑ ጥቅምት ወር ተገፍቷል። ለወትሮው በሺዎች የሚቆተሩ ተሳፊዎችን ይዞ በጎዳናዎች ላይ ይደረግ የነበረው ውድድር ዘንድሮ ሴንት ጀምስ በተሰኘው የከተማዋ መነፈሻን 20 ጊዜ በመዞር ተፈጽሟል።
40ሺ ተሳታፊዎች በመረጡት ስፍራ በያሉበት በርቀት ሮጠዋል። ውድድሩን በመጨረሳቸውም ኦፌሴላዊ ሜዳሊያ ይቀበላሉ።የሚያዚያ ውድድር በመሰረዙ ምክንያት ኢኮኖሚያዊ ችግር ለገጠማቸው ግብረሰናይ ድርጅቶችም በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብ ይሰባሰባል ተብሏል።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
ክሪኬት:-
የህንድ ክሪኬት ፕሪሜር ሊግ ተጨዋቾች የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ አምራቾችን የንግድ ምልክት በመለዮቸው ላይ አትመው ለመጫወት ተስማምተዋል።
ቅዳሜ በሚጀመረው የውድድር ወቅት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጀምሩ የተዋቀ ሲሆን እርምጃው የወር አበባን በተመለከተ በሀገሬው ዘንድ ያለውን የተሳሳተ ምልከታ ለመዋጋት እንደሚያግዝ ተስፋ ተጥሎበታል።
ራጃስታን ሮያልስ የተባለው ቡድን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ከሚያመርተው ኒኒ ኪባንያ ጋር ስምምነት በመፈጸም የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል።
«ይሄ ርዕስ በህንድ እና በብዙ የዓለማችን ሀገራት ነውር ነው። ህንድ ውስጥ ጉዳዩን በተመለከተ አጠቃላይ የግንዛቤ ችግር አለ።ወንዶች ብቻ ሳይሆን ወንዶች ላይም » ብለዋል የክለቡ የእንቅስቃሴ(ስምሪት) ሃላፊ ።በደቡብ እስያ ለሚኖሩ ሴቶች፣ በተለይ ለታዳጊ ወጣት ሴቶች- የወር አበባ ጉዳይ የሚያሳፍር እና ምቾት የማይሰጥም ነው።