በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዕምነት ተቋማቱ ህጋዊ ሰውነት ስለሰጡት አዋጆች የሃይማኖት አባቶች ምን ይላሉ?


ከግራ ወደ ቀኝ ኡስታዝ አህመድ ጀበል እና ፓስተር ሀንፍሬ አሊጋዝ
ከግራ ወደ ቀኝ ኡስታዝ አህመድ ጀበል እና ፓስተር ሀንፍሬ አሊጋዝ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 05 ቀን ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትን እና የወንጌል አማኞች አብያተ-ክርስቲየናት ምክርቤትን ህጋዊ ሰውነት የሚያጎናጽፉ ሁለት አዋጆችን አጽድቋል።

አዋጅ 1206 / 2012 ለኢትዮጵያ እስልምና ምክር ቤት ህጋዊ ዕውቅናን የሰጠው አዲስ አዋጅ ቁጥር ነው።

ይህ አዋጅ ይወጣ ዘንድ የዕምነቱ ተከታዮች ዓመታትን በወሰደ ጥረት ውስጥ ማለፋቸውን የሚያስታውሱት የታሪክ ተመራማሪውና በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የቅርብ ጊዜ ትግል ውስጥም ስማቸው በቀደምትነት ከሚነሱት መካከል አንዱ የሆኑት ኡስታዝ አህመድ ጀበል፣ አዋጁ ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ)የሚገባውን ዕውቅና መሰጠቱን በበጎ ያነሳሉ ሆኖም «አዋጁ ብቻውን በቂ አይደለም!» ይላሉ። ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፣«እስከዛሬ ሲነሱ ለነበሩ፣ ለወደፊቱም ለሚነሱ (የመብት ጥያቄዎች ) መሰረት ጥሏል።ሆኖም ሁሉ ነገር አለቀ ማለት ግን አይደለም» ሲሉም አክለዋል።

ሰኔ 5 /2012 የኢትየጵያ ፓርላማ ካጸደቃቸው አዋጆች ሌላኛው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ- ክርስቲያናት ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ያላበሰው አዋጅ ቁጥር 1307/2012 ይገኝበታል ነው።

የዓለም አቀፍ ኢትዮጵያዊያን ኢቫንጀሊካል ቤተ-ክርስቲያን ዋና ፓስተር ሃንፍሬ አሊጋዝ የዕምነቱ ተከታዮች እዚህ ቀን ላይ ከመድረሳቸው በፊት ድምጻቸውን የሚያሳሙበት ተቋም፣ ዕምነታቸውን በነጻነት የሚከተሉበት ሁኔታ ለመፍጠር በሞከሩባቸው ዘመናት ውስጥ ያየቸውን ፈተናዎች አውስተው ለዚህ ቀን መድረሳቸው የፈጠረባቸውን ደስታ ለአሜሪካ ድምጽ አጋርተዋል።

ፓስተር ሃንፍሬ አሊጋዝ የአሁኑ አዋጅ ከሚፈጥራቸው መልካም ውጤቶች አንዱ የዕምነቱ ተከታዮች ለትውልድ ሀገራቸው ሊያደርጓቸው የሚፈልጓቸውን በጎ ስራዎች በተሻለ ተነሳሽነትት እንዲፈጽሙ የሚያበረታታ ስለመሆኑም ያስረዳሉ።

ለመሆኑ በሃይማኖቶቹ ተከታዮች ዘንድ ለዓመታት ቅሬታን ፈጥረው የነበሩት አሰራሮች የትኞቹ ናቸው?የአዲሶቹ አዋጅ ፋይዳስ ምንድነው? የሚሉትን እና ሌሎች ጥያቄዎችን የሚመልሰውን አጭር መሰናዶ ያዳምጡ።

ለዕምነት ተቛማቱ ህጋዊ ሰውነት ስለሰጡት አዋጆች የሃይማኖት አባቶች ምን ይላሉ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:15 0:00


XS
SM
MD
LG