በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መጽሃፍትን በዩቲዩብ ፦ቆይታ ከማርታ ኃይለየሱስ ጋር


ማርታ ኃይለየሱስ
ማርታ ኃይለየሱስ

የቴሌቭዥን መስኮት ለሚያዘወትር ሰው ማርታ ኃይለየሱስ እንግዳ አትሆንበትም። "ደርሶ -መልስ" በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ በነበራት የትወና ተሳትፎ ያስታውሳታል።

የመጽሃፍትን መንደር ለሚያስስ ሰውም ማርታ አዲስ አትሆንበትም ። "ማሬ -መጽሃፍት" በተሰኘ ድርጅቷ በኩል ለአንባቢያን መጽሃፍትን በያሉበት አድርሳለች። አሁን ደግሞ የማህበራዊ መገናኛዎችን በተለይ ደግሞ የዩቱዩብ አውታርን ከሚጎበኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር የሚያቀራርባት አዲስ ጥረት ጀምራለች።

በአዲሱ የዩቲዩብ አምዷ አዳዲስ እና ነባር መጽሃፍትን ታስተዋውቃለች፣ ማራኪ አንቀጾችን ለአድማጮች ታሰማለች፣ መጽሃፍት እና ንባብ ላይ ያነጣጠሩ ምልከታዎቿንም ታጋራለች።

በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሀብታሙ ስዩም ከማርታ ኃይለየሱስ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።

መጽሃፍትን በዩቲዩብ ፦ቆይታ ከማርታ ኃይለየሱስ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:41 0:00


XS
SM
MD
LG