በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የክልል ልዩ ኃይሎች አነጋጋሪ ምስረታ እና ስጋት(ውይይት)


የትግራይ ፣አሮሚያ እና አማራ ክልሎች ልዩ ኋይሎች በከፊል
የትግራይ ፣አሮሚያ እና አማራ ክልሎች ልዩ ኋይሎች በከፊል

የሀገር እና ህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ ከተቋቋሙት የሀገር መከለከያ ሰራዊት ፣ የፌዴራል እና ክልል ፖሊስ ኃይሎች በተጨማሪ ፣ በየክልሉ የሚገኙ የልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ ተቋማት ይጠቀሳሉ።

የልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ ተቋማት ምስረታ ህገመንግስታዊነት እና ተልኳቸውን የሚያከናውኑበት መንገድ የሙግት መነሾ ከሆነ ሰነባብቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭቶች መበራከታቸው፣የተለያዩ ክልሎች የልዩ ኃይል ስልጠናዎችን ማከታተላቸውን ተከትሎ ሙግቱ እንደ አዲስ ተቀስቅሷል።

እኛም በኢትዮጵያ ወቅታዊ እና መጻኢ የሰላም ሁኔታ ውስጥ የእነዚህን ተቋማት ሚና ምን መምሰል እንዳለበት ለመነጋገር ተከታታይ የውይይት መርሀ-ግብሮችን እናስደምጣለን።

ለዛሬ ሶስት ተወያዮችን ይዘን ቀርበናል።ተወያዮቻችንን እንተዋወቅ፦

አቶ ፍሬ ህይወት ሳሙኤል፦ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሰርተዋል። በምርጫ 97 ማግስት የተከሰቱ ግጭቶችን ይዘት እንዲያጣራ የተቋቋመው ኮሚሽን ሊቀመንበርም ሆነው አገልግለዋል።በአሁኑ ሰዓት በዚህ በዮናይትድ ስቴትስ ነዋሪ ናቸው።

ብርጋዴር ጄኔራል ካሳየ ጨመዳ፦ ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ በቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ውስጥ በከፍተኛ አመራርነት ያገለገሉ፣ በጦር ትምህርት ቤት እና ጦር ሜዳ ውሏቸው ያካበቷቸውን ልምዶች አሁን ድረስ ለኢትዮጵያዊያን በተለያዩ መልኮች በመጽሃፍ እያከፋሉ የሚገኙ ናቸው።

አቶ ስዩም አሰፋ ፦ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄዱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ክንውኖችን በንቃት የሚከታተሉ፤በቅርቡ የጎሳ ፖለቲካ በህግ ይታገድ ፣ የልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ እንዲኖር የሚጠይቁ ዘመቻዎችን ያስተባበሩ ናቸው።

በዚህ የመወያያ ርዕስ ላይ የመጀመሪያ ዙር ተወያዮች ሆነው ስለቀረቡ በአድማጮች ስም እናመሰግናለን።

ውይይቱን ያዳምጡ።

የክልል ልዩ ኋይሎች አነጋጋሪ ምስረታ እና ስጋት (ውይይት)
please wait

No media source currently available

0:00 0:32:30 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG