ዋሽንግተን ዲሲ —
በአዲሲቱ ሀገር ደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት ሳልቫ ኪርና ምክትላቸው በነበሩት ሪየኽ ማቻር መካከል የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ የዘር ክፍፍል መቀስቀሱ አልቀረም። ፕረዚዳንት ኪር ከዲንቃ ዘር ሲሆኑ Mr. ማቻር የኑየር ጎሳ አባል ናቸው።
ከሁለት ሳምንታት በፊት ቅዳሜ በተደረገው የገዢው ፓርቲ የሱዳን ህዝባዊ ሐርነት ንቅናቄ ስብሰባ ግጭት ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሳያልቁ እንዳልቀሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣኖች ገልጸዋል።
የደቡብ ሱዳንኑ ርእሰ ብሄር ባለፈው ሀምሌ ወር ላይ ከምክትል ፕረዚዳንትነት ስልጣናቸው የተባረሩት ሪያኽ ማቻር የመፈንቅለመንግስት ሴራ ጠንስሰዋል ሲሉ ይከሳሉ። Mr. ማቻር ግን ስልጣን ለመያዝ አልሞከርኩም በማለት አስተባብለዋል። ነገር ግን የሀገሪቱ ወታደራዊ ሀይል ፕረዚዳንት ኪሪን ከስልጣን እንዲያወርድ ጥሪ አድርገዋል።ያም ሆነ ይህ ከአስሩ የደቡብ ሱዳን ክፍላተ-ሀገር ግማሽ ወደሚሆኑት ግጭት ተስፋፍቷል።
ፕረዚዳንት ኪርና Mr. ማቻር ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት የመነጋገር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። ፕረዚዳንቱ ካለምንም ቅድመ-ግዴታ እነጋገራለሁ ሲሉ Mr. ማቻር ግን መጀመርያ የታሰሩት ደጋፊዎቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።