በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


የኅዳሴ ግድብ ንድፍ
በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፓብሊሲቲ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ “ህዳሴ ግድብን ከመገንባት የሚያቆመው የለም” ሲሉ ባስታወቁበት በአሁኑ ወቅት የግብጽ ባለስልጣኖች በመልካም ጉርብትና ላይ በማትኮር ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እየሞከሩ ነው ሲል አሶሸትድ ፕረስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ግብጽ ከአፍሪቃ ትልቁ ግድብ ሲገነባ የአባይን ውሀ ሊቀንስ ይችላል የሚል ስጋት ያላት ቢሆንም ግብጽ ኢትዮጵያን ታከብራለች። ማንኛውንም አይነት የማጥቃት እርምጃም አትወስድም ሲሉ የግብጹ ፕረዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ እንዳስታወቁ አሶሼትድ ፕረስ ጠቁሟል።

ባለፈው ረቡዕ የወጣ የግብጽ ካቢኔ መግለጫ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በመልከም ጉርብትናና በመከባበር፣ አንደኛዋ ሌላዋን ሳትጎዳ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ ግንኙነትን ለማጠናከር በጉጉት ትጠብቃለች ይላል።

መግለጫው አያይዞም ግብጽ የኢትዮጵያን የልማት አስፋላጊነት ትረዳለች። ኢትዮጵያ የግብጽን የውሀ ጥቅም እንደማትጎዳ በተደጋጋሚ የሰጠችው ማረጋገጭንም ትገነዘባለች። ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር በፍጥነት “የፖለቲካና የቴክኒካዊ ንግግር" ማካሄድ ትፈልጋለች ማለቱን አሶሼተድ ፕረስ ጠቅሷል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-6-7-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG