በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ
ጥንታዊትዋ የቅድመ-ሰው ቅሪት አካል ሉሲ ወይም ድንቅነሽ ከአምስት አመታት የ United States ቆይታ በኋላ ባለፈው ረቡእ ወደ ሀገርዋ ተመለሰች ሲል CBS የተባለው የ United States ቴሌቪዥን ድረ-ገጽ ዘግቧል።

የ3.2 ሚልዮን እድሜ ያላት ሉሲ እአአ በ 1974 አም የተገኘችው Donald Johansen በተባሉ አሜሪካዊ የሳይንስ ጠቢብ በሚመሩ የአርኪዮሎጂስቶች ቡድን ሲሆን የአስትራሎፒተኩስ አፈረንስስን 40 ከመቶ ቅሪት አካልን እንደምትይዝ ተገልጾ ነበር። ሉሲ የሚል ስም የተሰጣትም “Lucy in the sky with diomonds” ከሚለው የቢትልስ ዘፈን ነው። ሙዚቃው በወቅቱ የሉሲን መገኘት ለማክበር የተሰማ ነበር ይላል የ CBS ዘገባ።

በሌላ ዘገባ ደግሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ነዳጅ ዘይት ተገኘቷል የሚለው ወሬ አሳሳች ነው ማለታቸውን ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዘገቧል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስርት ይህን የተናገሩት Tullow Oil የተባለው የነዳጅ ዘይት ኩባንያን በሚመለከት ነው። የነዳጅ ዘይት ኩባንያው የነዳጅ ዘይት ምልክት ማግኘቱን ቢናገርም ነዳጅ ዘይት ለማምረት የሚያስችለውን ያህል የኢኮኖሚ ብቃይ ይኖረዋል ማለት እንዳልሆነ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ማስገንዘባቸውን ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ገልጿል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-5-3-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG