በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


theguardian የተባለው የብሪታንያ ጋዜጣ ድር-ገጽ ላይ የወጣ ጽሁፍ ኢትዮጵያ እንደማንኛቸውም የሰምጥ ሸለቆ ሃገሮች ሁሉ ትልቅ የgeothermal energy ማለት ከምድር በታች ከሚገኝ ሙቀት ኤነርጂ የማፍለቅ መሰረት አላት። ይሁንና እስካሁን ባለው ጊዜ የሚያስፈልገው ወጪና በሙያው የሰለጠኑ ሰዎች ጉዳይ ችግር ሆኖ ቆይቷል ይላል።

አሁን ግን የኢትዮጵያ የልማት ባንክ በቀጣዮቹ አምስት ወራት ውስጥ በሀገሪቱ የግል ዘርፍ ከመሬት ሙቀት የሚገኝ ኤኔርጂ ውጥን ለመጀመር $20 ሚልዮን ዶላር እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ይህም በአለም ባንክ ወጪ የሚንቀሳቀስ ፕሮግራም አካል እንደሆነ። ኋላ ደግሞ ተጨማሪ $20 ሚልዮን ዶላር ለኤነርጂው ውጥን እንደሚጨመር ጽሁፉ ያወሳል።

IRIN የተባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳይ ዜናና ትንተና አገግሎት ደግሞ ምርታቸውን በደላሎች በኩል በመሸጥ በድህነት ይኖሩ ከነበሩት የኢትዮጵያ አነስተኛ የነጭ ቦለቄ አምሮቾች መካከል የተወሰኑት ገበያ ለማግኘት እንደቻሉ ያወሳል።

ለዘላቂ የንግድ ግንኙነት አዲስ የንግድ ሞዴል የተባለ ውጥን ህብረ ብሄራት የሆኑ የምግብ ኩባንያዎችን በአፍሪቃ አነስተኛ ይዘት ካልቸው ኩባንያዎች ጋር በማገናኘት ተግባር ስለረዳችው 15,000 የሚሆኑ ነጭ ቦሌቄ አምራች ገበሬዎች የተሻለ ምርት በማቅረብና በአነስተኛ ህብረት በመሰባሰብ የውጭ ገበያ ተደራሽነት ለማግኘት በቅተዋል ይላል IRIN።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-2-15-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG