በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወጣቷ ማህሌት XO ምግብ ቤት በመቐለ


ማህሌት ሃብተማርያም
የ21 ዓመቷ ማህሌት ሃብተማርያም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪት ናት፡፡ ማህሌት መቐለ በሚገኘው ፖሊ የቴክኖሎጂ ተቋም የስነ ህንጻ ትምህርትም ትማራለች፡፡ ሁለተኛ ዓመቷ ነው፡፡

ማህሌት ጊዜዋ በትምህርት ብቻ ማዋልን ኣልመረጠችም፡፡ መቐለ ከተማ ውስጥ በኣክሱም ሆቴል ኣጠገብ የሚገኘው XO (Hug and Kiss) ምግብ ቤት ባለቤትና ስራ ኣስከያጅም ናት፡፡ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞች እንግዶችና የውጭ ዜጎች በዚሁ ምግብ ቤት በሚዘጋጀው በርገርና ፒሳ ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡

ቤቱ ግድግዳ ውስጥ የተሰቀሉት የእህቷ የስእል ውጤቶች የተመጋቢውን የምግብ ኣምሮትን ይጨምራሉ፡፡ በጣም ለየት ባለ ቅርጽ የተገጣጠመው ወንበርና ጠረቤዛ የማህሌት የፈጠራ ውጤት ነው፡፡
ትምህርትና ስራ ባንድ ላይ ኣጣምሮ ማስኬድ ቀላል ኣይደለም ቢሆንም ግን ፍላጎት ካለ ስራና ትምህርት ኣቀናጅቶ ማስኬድ ኣይከብድም ብላለች ማህሌት፡፡

ኣዲስ ኣበባ ውስጥ ነው ተወልዳ ከእናቷና እህቷ ጋር ያደገችው ማህሌት ከእግእዛብሔር በኋላ ኣርኣያ የሆነችኝ በጣም ጠንካራዋ እናቴ ናት በማለት ለዛሬው የጥንካሬዋ ምንጩን ትገልጻለች፡፡

በ XO (Hug and Kiss) ምግብ ቤት ውስጥ 20 ወጣቶች ይሰራሉ፡፡ በቅርብ የምታግዛት በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት የህክምና ትምህርት እህት ኣለቻት፡፡ ሌሎች የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጓደኞቿም ነጻ ኣገልግሎት በመስጠት ያግዟታል፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:07:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG