ምሥራቅ ዩናዩትድ ስቴትስን ከትናንት በስተያና ትናንት የመታው ብርቱ ማዕበል ወይም ሃሪኬን የኒው ዮርክ ከተማን ስፋት ያለው አካባቢ አጥለቅልቆ በሺሆች የሚቆጠሩ ቤቶችን ያለኤሌክትሪክ ኃይል አስቀርቷል፡፡
አሁን ሃሪኬኑ ካለፈ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ኒው ዮርክ ምን ትመስላለች?
በሌላ በኩል ደግሞ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለምርጫ ቅስቀሣ ቁልፍ ወደሆነችው ኦሃዮ ሊያደርጉ የነበረውን ጉዞ አቋርጠው በማዕበሉ ክፉኛ ከተመቱት ግዛቶች አንዷ የሆነችውን ኒው ጀርሲን ዛሬ ይጎበኛሉ እየተባለ ነው፡፡
መንግሥት ፈጥኖ እንደሚንቀሣቀስ እና ለተጎዱት አካባቢዎች እገዛው በተሣካ ሁኔታ እንደሚደርስም ፕሬዚዳንቱ ቃል ገብተዋል፡፡
የፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ተፎካካሪ የሆኑት የሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩ ሚት ራምኒም ትናንት በኦሃዮ ግዛት ሊያካሂዱ የነበረውን የምረጡኝ ዘመቻ አቋርጠው ለተጎዱት የታሸጉ ምግቦችን ሲያሰባስቡ ውለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ በበረታው ማዕበል ውስጥ በዓለም ዙሪያ በ43 ቋንቋዎች የሚያሠራጫቸውን ፕሮግራሞች ሣያቋርጥ ማስተላለፉን የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች አድንቀዋል፡፡