በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጥንታዊውን የበገና አደራደር በኢንተርኔት ላይ ለማስተማር እየጣረ ያለው ወጣት -ምጥን ቆይታ


መምህር አቤል ተስፋዬ
መምህር አቤል ተስፋዬ

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንት ተከታዮች ዐቢይ( የፋሲካ) ጾም ጀምረዋል።ለቀጣይ ሁለት ወራት ጽሞና እና ጸሎት፣ የሚነግስባቸው ጊዜያትን እንደሚያሳልፉ ይጠበቃል።

እንደዚህ ባለው ጊዜ በተደጋጋሚ ከሚሰሙት መንፈስ አረጋጊ የሙዚቃ መሳሪያዎች አንዱ በገና ነው።በቀደመው ጊዜ ይሄንን መሳሪያ ለመማር በጣት ከሚቆጠሩ የበገና ደርዳሪዎች መጠጋት፣ ከበድ ያለ የመማር ማስተማር ዘይቤ ማሰለፍ ይጠይቅ ነበር።

አንድ ወጣት ግን አስቸጋሪውን መንገድ በተወሰነ ደረጃ ለመቀየር ተነስቷል።ወጣቱ መምህር አቤል ተስፋዬ ይባላል፣ ከአንጋፋ የበገና ደርዳሪዎች ጋር በመሆን በበይነ -መረብ ላይ የበገና አደራደር ክፍሎትን፣ ከትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ ዳራው ጋር እያስማማ በማስተማር ላይ ይገኛል።

ሙሉ ጥንቅሩን ያዳምጡ

የበገና አደራደር በኢንተርኔት ላይ ከሚያስተምረው መምህር አቤል ተስፋዬ ጋር የተደረገ ቆይታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG