በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋቢና ቴክ፡-ጓዝ ጠቅላዩ “ባልደራሱ”


Balderasu
Balderasu

አዲስ አበባን በመሰሉ ከተሞች ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ ቤት ለመቀየር አስበው ፣አሊያም በከተማዎ ሌላኛ ጫፍ ላይ ለሚገኝ ሰው በፍጥነት የሚደርስ ጥቅል ኖሮዎት -በፍጥነት አድራሽ ማግኘት ቀላል የማይባል ልፋት አለው፡፡

በተሰባጠረ ሁኔታ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች፣የዋጋ ሙግት እና የሚጋዘው ሸቀጥ (ቁሳቁስ) ደህነት አጠራጣሪነት የደንበኞች ቅሬታ ምንጭ ሆኖ ሰንብቷል፡፡

ከሰሞኑ ብቅ ያለ አንድ አገልግሎት ግን መሰል ሁነቶችን እንደሚቀይር ፈጣሪዎቹ ተስፋ ጥለውበታል፡፡

“ ባልደራሱ” የተሰኘው አገልግሎት ደንበኞች፣ ዕቃ ጫኝ ተሽከርካሪዎችን በቀላሉ አግኝተው ጥቅል ጓዞቻቸውን(መልዕክቶቻቸውን) ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላኛው በፍጥነት ማንቀሳቀስ እንዲያስችል የተዘጋጀ ስለመሆኑ ሰምተናል፡፡

ከአራት ዓመት በፊት ራሱ ባዘጋጃቸው ተሽከርካሪዎች መሰል አገልግሎቶችን ሲሰጥ የሰነበተው ሆራይዘን ኤክስፕረስ ድርጅት ፣አሁን ላይ ማናቸውም ዕቃ ጫኝ መኪኖች ያላቸው ሰዎችን እና ደንበኞችን የሚያስተሳስር ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

ሀብታሙ ስዩም ከድርጅቱ የቴክኒክ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሶፎንያስ እምቢበል ጋር ያደረገውን አጭር ቆይታ ያዳምጡ፡፡

ጋቢና ቴክ:ጥቂት ስለ "ባልደራሱ"
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:19 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG