ዋሽንግተን ዲሲ —
የባይደን አስተዳደር በአውቶሚክ ፕሮግራም ሳቢያ በኢራን ላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ለማላላት መወሰኑን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡
ይህ የሆነው እኤአ በ2015 ከኢራን ጋር ተደርጎ የነበረውን የኒዪክለየር ስምምነት መልሶ ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገው ድርድር እልባት ሊሰጠው እየተቃረበ በመጣበት ወሳኝ ጊዜ ውስጥ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ተደራዳሪዎች የመጨረሻውን የድርድር ፍጻሜ ለመቋጨት ትናንት ዓርብ ወደ ቪየና ማምራታቸው ተገልጿል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከኢራን የኒዪከለየር ፕሮግራም ጋር ተያይዞ የተጣሉት በርካታዎቹ ማእቀቦች እንዲነሱ በሚያዘው ትዕዛዝ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩትም ትላንት ዓርብ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
እኤአ በ2018 በቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፈርሶ የነበረው ስምምነት በዚህኛው ድርደር ተመልሶ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነገሯል፡፡