ዋሽንግተን ዲሲ —
ዶ/ር ኤርሚያስ ካቻ እና ዶ/ር ፍጹም ጥላሁን መኖሪያቸውን በዮናይት ስቴትስ ያደረጉ የህክምና ባለሙያዎች ናቸው።ውጥረት እና የሰዓት ጥበት ከማያጣው ስራቸው አስተርፈው «የጤና ወግ» የተሰኘ የበይነ-መረብ ላይ የመረጃ አውታር አቋቁመዋል።
አውታሩ ጤና ነክ መረጃዎችን ከማቀበል አልፎ፣ አሳሳች የጤና መረጃዎችን በማምከን እውነተኛ መረጃዎችን ለበይነ-መረብ ጎብኝዎች ለማሰራጨት ወጥኗል።
ስለ አውታሩ ጅማሬ ፣ የመጪ ዘመን ውጥን እና ተዛማጅ ጉዳዮች የተጨዋወትንበትን ቆይታ ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ