በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋንሪያ መንገድ ፤ ሙዚቃን ለማህበረሰባዊ ንቃት


Wanria Abala

ለሙዚቀኝነት ብዙም ክብር ከማይቸር ማህበረሰብ መውጣቷን የምትናገረው ዋንሪያ አባላ፣በቅርቡ በእኝዋክኛ የተጫወተቻቸው ሙዚቃዎች መልካም ምላሽ እያስገኙላት ነው፡፡

ሙዚቃን ከተለመዱ ጉዳዮቸ ይልቅ የማህበረሰብ ኅጸጾችን ለመንቀስ እንደምትጠቀምበት የምትናገረው ወጣት ከያኒ የእሷ እና መሰል ወጣቶች የሙዚቃ ዓለም ጥረቶች ግን ፈተና የሞላበት እንደሆነም ታነሳሳለች፡፡

ጋምቤላ የተወለደችው እና ፣በአሁኑ ሰዓት የአምቦ ዩኒቨርሰቲ ተማሪ የሆነቸው ዋንሪያ ከሀብታሙ ስዩም ጋር ባደረገችው ቆይታ ተጨማሪ ጉዳዮችንም አንስታለች፡፡

ቆይታቸው የሚጀመረው ፣ማህበረሰቧ የሚያውገዘውን የሙዚቀኝነት የስራ ዘርፍ ለምን እንደመረጠች በምታብራራበት አፍታ ነው፡፡

የዋንሪያ መንገድ ፤ ሙዚቃን ለማህበረሰባዊ ንቃት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG