ዋሽንግተን ዲሲ —
ኦባላ ኦባላ በሜኔሶታ ግዛት -ኦስቲን ከተማ ምክር ቤት አባል ለመሆን ተወዳድሮ ያሸነፈ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነው። ገና የአሜሪካ ዜግነቱን ባገኘ በዓመቱ ለዚህ ድል የበቃው የ27 ዓመቱ ወጣት እዚህ ከመድረሱ በፊት ብዙ ውጣውረዶችን አይቷል።
በኦስቲን ግዛት ታሪክ ለየት ያለው ድሉ ለብዙ ስደተኞች ተስፋን እንደሚፈነጥቅም ይናገራል። ከኦስቲን ከተማ ምክር ቤት አባል ኦባላ ኦባላ ጋር አጭር ቆይታ ያደረገው ሀብታሙ ስዩም ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል።