በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ቲያትር ቤቶች ፈተና


Ethiopian National Theater
Ethiopian National Theater

ለኢትዮጵያ የኪነጥበብ እድገትና ዛሬ ላለበት ደረጃ መሰረት የጣሉት አንጋፋ ቲያትር ቤቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ተዘግተው በመቆየታቸው ሙያውና ሙያተኞች ትልቅ ችግር ላይ ወድቀዋል። ቀድሞውንም በተመልካች ማነስና በአማራጮች መበራከት ምክንያት ፈተናዎች የበዙበት የቲያትር ሙያ ኮሮና ይበልጥ አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተው የቲያትር ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

የኢትዮጵያ ቲያትር ቤቶች ፈተና
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:01 0:00

የተለያዩ የመድረክ ቲያትሮችና ድራማዎች ፀሀፊ እንዲሁም ጋዜጠኛ የሆነው ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ በሙያው ለቲያትር ካለውቅርበት በተጨማሪ ከ 20 አመታት በላይ ባለመታከት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚወጡትን ቲያትሮች ተመልክቷል። ቴዎድሮስለመጨረሻ ግዜ ቲያትር ያየው ግን የዛሬ ሰባት ወር በሀገር ፍቅር ይታይ የነበረውንና እነ ፋንቱ ማንዶዬን የመሳሰሉ አንጋፋተዋንያን የተሳተፉበትን 'ሰዓት እላፊ' የተሰኘውን ቲያትር እንደነበር ያስታውሳል።

ብዙ ተወዳጅ ድምፃውያንና ተዋንያንን የፈጠሩትና ለትልቅ ደረጃ ያበቁት አንጋፋዎቹ የኢትዮጵያ ቲያትር ቤቶች ግን በኮሮናቫይረስ ምክንያት ላለፉት ሰባት ወራት በመዘጋታቸው ከተመልካች ጋር ተራርቀው ሰንብተዋል። ቲያትር በማሳየትና አዳራሽበማከራየት ያገኙት የነበረው ገቢ በመቋረጡም ቲያትር ቤቶቹም ሆኑ ሙያተኞቹ ለችግር ተጋልጠዋል።

በሳምንት ስምንት ቲያትሮችን ያሳይ የነበረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቲያትር የቲያትር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደስታአስረስ እንዳስረዱን፣ ቲያትር ቤቶቹ ከመንግስት በሚመደብ በጀት የሚተዳደሩ በመሆናቸው ቋሚ የቲያትር ቤቱ ተቀጣሪዎችደሞዝ ባይቋረጥባቸውም፣ አንድ ቲያትር ለመታየት ከተመልካች በሚገኘው ገቢ የራሱን ወጪ መሸፈን ይኖርበታል። ከውጪየሚመጡ በርካታ ተጋባዥ ተዋንያንም የሚከፈላቸው ከተመልካች በሚገኝ ገቢ ነው።

በተመሳሳይ በሳምንት ስምንት ቲያትሮችን ያሳይ የነበረው የሀገር ፍቀር ቲያትርም በኮሮና ምክንያት ከተዘጋ ወዲህ ከተመልካችእና አዳራሽ ኪራይ ያገኝ የነበርው ገቢ ሙሉ ለሙሉ በመቋረጡ ባለሙያውም፣ ሙያውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉየቲያትር ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልከሪም ጀማል ይገልፃሉ።

ከቲያትር ተመልካችነቱ ባለፈ ብዙ ቲያትሮችን በመፃፍና በማዘጋጀት የሚታወቀው ቴዎድሮስ ተክለአረጋይም በኮሮና ምክንያትብዙ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ገቢያቸው በመቋረጡ እየደረሰባቸው ያለውን የኢኮኖሚ ጫና እንዲህ ይገልፀዋል።

በእርግጥ የኮሮና ቫይረስ ተጨማሪ ተግዳሮቶችን ይዞ መጣ እንጂ፣ የቲያትር ሙያ ኢትዮጵያ ውስጥ ፈተና መጋፈጥ ከጀመረቆየት ብሏል። በቴክኖሎጂ ማደግና አማራጭ መብዛት ምክንያት የተመልካች መቀነስ፣ ለዘርፉ በቂ ትኩረት አለመስጠትና፣የሙያተኛው ለስራው ያለው ተቆርቋሪነት ዝቅተኛ መሆን የቲያትር ዘርፉን ቀድሞም እየተፈታተነው እንደነበር ቴዎድሮስያስረዳል።

በዚህ ሀሳብ የሚስማሙት የብሄራዊ ቲያትር ሀላፊው አቶ ደስታም የኮሮና ቫይረስ ለዘርፉ ተጨማሪ ፈተና ነው ይላሉ።

ከሰባት ወር መዘጋት በኃላ አንዳንድ ሲኒማ ቤቶች ፊልሞችን ማሳየት ጀምረዋል። የመድረክ ስራ ግን በመድረክ ላይለሚተውኑትም ሆነ ከመድረክ ጀርባ ሆነው በቴክኒክና በመስተንግዶ ለሚያግዙ ባለሙያዎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግንስለሚጠይቅ በምን መልኩ መከፈት እንደሚችሉ ውይይት እየተደረገ መሆኑን አቶ አብዱልከሪም ያስረዳሉ።

በቲያትር ዘርፉ ዙሪያ የተጋረጠው ፈተና ኮቪድ 19 ያስከተላቸውን ፈተናዎች በመቋቋም ብቻ የሚፈታ አለመሆኑን ግንባለሙያዎቹ ይስማሙበታል። ቲያትር ቤቶቹ ብቻ ሳይሆኑ መንግስትን ጨምሮ አጠቃላይ የኪነጥበብ ባለሙያው ተረባርቦመሰረታዊ ለውጦችን በማምጣት ሙያውን ከአደጋ መታደግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG