በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው ስቴዲዮም አርክቴክት ተቃውሟችን አሰሙ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምንም ወቀሱ


.
.

የቤጂኒንግን የክረምት ኦሎምፒክ ከሚስተናገድበት ስታዲየም ግንባታ በስተጀርባ ያለው ታዋቂው የቻይናው አርትኬት፣ አይ ዌዊ፣ ትናንት ዓርብ በበዐሉ መክፈቻ ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግሥታቱ የዓለም ጤና ድርጅት ድሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ “ስለኮቪድ 19 ወረርሽኝ መንስኤ ጠንካራ ጥያቄዎችን ባለማንሳታቸው ቻይና የወርቅ ሜዳልያ ልትሸልማቸው ይገባል” ሲሉ መሳለቃቸው ተዘገበ፡፡

ዌዊ ለአሶሼይትድ ፕሬስ በሰጡት ቃለ መጠየቅ ቻይና ውስጥ ብዙም ባልተለመደ መንገድ ቻይናን በሰብዊት መብት አያያዝና ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ የሰጠችው ምላሽን በማንሳት ተችተዋል፡፡

ዌዊ በመክፈቻው ላይ የኦሎምፒክ ነበልባል ችቦ ይዘው፣ በቀይና ነጭ ቤጂንግ ኦሎምፒክ 2022 የሚል የክረምት ልብስና የሱፍ ቆብ ለብሰው፣ በትዊት ገጻቸው ላይ የራሳቸውን ፎቶግራፍ የለጠፉትን የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ወቅሰዋል፡፡

“ኦ ስለ እግዚአብሄር! እኝህ ሰው ከቻይና የወርቅ ሜዳልያ ማግኘት አለባቸውም፡፡ ምክንያቱም ምንም ዓይነት ትክክለኛ ጥያቄ ጠይቀው አያውቁም” ሲሉ ተሳልቀዋል፡፡ የጤና ባለሙያዎች የህዝቡን ጤና መከላከል ይገባቸው ነበር ያሉት ዌዊ “እኝ ሰው ህሊናቸው የት አለ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ዶር ቴዎድሮስ በቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደርም ወረርሽኙ ለመጀመሪያ ጊዜ በቻይና ውሃን ከተማ በተከሰበት ወቅት ትክክለኛውን እምርጃ ባለመውሰዳቸውና ይልቁንም ቻይናን በማመስገናቸው ከፍተኛ ትችት ይደርስባቸው እንደነበር በዘገባው ተመልክቷል፡፡

ዘገባው የአሶሼይትድ ፕሬስ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG