ዋሽንግተን ዲሲ —
ዚምባቡዌን በፍጹም ቅጣት ምት በዕለቱ በረታው የኢትዮጵያ ቡድን ውስጥ ከነበሩት መካከል ጆሯችን ውስጥ ዛሬም ድረስ የሚያቃጭሉ ስሞቸ አሉ፡፡
ይሄ ከፊት ለፊቴ የተቀመው ሽበት ጣል ጣለ ያደረገበት፣የስፖርትኛ ቁመናው ዛሬም ያልተለየው ጎልማሳ የዚያ ባለታሪክ ቡድን አባል ነበር፡፡
ለጌቱ ከበደ ፣ያ ውድድር ያተመው ትዝታ በቀላሉ የሚፋቅ አይደለም፡፡