በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰው ልጆችን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስ ስላለመው ቴሌስኮፕ


.
.

ዩናይትድ ስቴትስ በምድር ላይ ክብደቱ ከ6000ኪ ግራም በላይ የሚመዝን ፣ ነገሮችን በእጅጉ አቅርቦ የሚያሳይ መሳሪያ (ቴሌስኮፕ) ወደ ህዋ ከሰሞኑ አምጥቃለች ።ስሙም የጄምስ ዌብ ሳተላይት ቴሌስኮፕ ይሰኛል ።

10 ቢሊየን ዶላር ገደማ ገንዘብ እንደፈሰሰበት የተነገረለት፣ የጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ ከሀሳብ ጥንሱሱ እስከ እውን ሆኖ እስከ መጠቀበት ቀን ድረስ ከ20 ዓመታት በላይ የተሻገረ ልፋትን ጠይቋል። የበርካታ ባለሙያዎች ርብርብም አስፈልጎታል ።

እንዲህ ያለው የቴክኖሎጂ እመርታ ፣ በአጠቃላይ በዘርፉ ውስጥ ካለው ጠቀሜታ ባሻገር፣ በተለያዩ የዓለም ጥጎች ለሚኖሩ ህዝቦች ያለውን እርባና የሚጠይቁ ጥቂት አይደሉም ። በየለት ህይወታችን ውስጥ ምን የተሻለ ነገር ይጨምራል ? ብሎ መጠየቅም አይቀሬ ነው ። እኒህና ሌሎች ተያያዝ ጥያቄዎችን ይመልሱልን ዘንድ ሀብታሙ ስዩም ዶ/ር ብሩክ ላቀውን አግኝቷቸዋል ።

ዶ/ር ብሩክ ላቀው በዩናይትድ ስቴትስ የጠፈር ምርምር ተቋም ውስጥ ከ30 ዓመታት አገልግለዋል። በቅርቡ ጡሮታ ከወጡ በኃላ በተለያዩ ኃላፊነቶች ለተቐሙ ሙያዊ አበርክቶታቸውን ቀጥለዋል ።

የቪዲዮ መሰናዶውን ይመልከቱ ።

የሰው ልጆችን የዘመናት ጥያቄ ለመመለስ ስላለመው የጄምስ ዌብ ቴሌስኮፕ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00

XS
SM
MD
LG