ዋሽንግተን ዲሲ —
ሰሞኑን በዮናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ታሪክ አዳዲስ ክስተቶች ተመዝግበዋል። የአሜሪካ ህግ መወሰኛ ምክር ቤት ኮንግረስ በተቃዋሚ ሰልፈኞች መወረሩ እና ምክር ቤቱ መደበኛ ስራውን ለሰዓታት እንዲያቋርጥ መገደዱ አንደኛው ክስተት ሲሆን። የጆርጂያ ግዛት የመጀመሪያውን ጥቁር የህዝብ እንደራሴ( ሴናተር) መምረጧ ደግሞ ሁለተኛው ክስተት ነው። ሁለቱ ክስተቶች ያላቸውን ፖለቲካዊ አንደምታ ለማወቅ ብሎም ለተዛማጅ ጥያቄዎች ማብራሪያ ፍለጋ ሀብታሙ ስዩም- ከፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል። በመቀጠል ይደመጣል።