ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ይጠበቁ ዘንድ ሰዎች ህዝብ ከሚበዛባቸው ስፍራዎች እንዲርቁ መታዘዙን ተከትሎ ከተቀዛቀዙ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች አንዱ የፊልም ዘርፍ ነው።
ለወትሮው በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችን ያስተናግዱ የነበሩ ሲኒማ ቤቶች ተዘግተዋል። የፊልም ቀረጻ ለማከናወን ሁኔታዎች የሚፈቅዱ አልሆነም። ፊልም ሰሪዎች ገቢ የሚገኙባቸው የተለመዱ መንገዶች ተመናምነዋል። በዋነኝነት በግለሰቦች ሁነኛ ጥረት ውስጥ ሲታትር የባጀው የሚገኘው የኢትዮጵያ ፊልም ዘርፍ አጣብቂኝ ፈታኝ ቀናትን እያሳለፈ መሆኑን እየተነገረ ነው።
ሄኖክ አየለ በበርካታ የኢትዮጵያ ፊልም አዘውታሪዎች ዘንድ የሚታወቅ ስም ነው። የወንዶች ጉዳይ 1 ፣ፔንዱለም ፣ዐልቦ እና ሌሎች በብዙሃን ዘንድ የተደነቁ ፊልሞችን አዘጋጅቷል። ከሰሞኑ አንድ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ቀረጻ ለማከናወን ዕቅድ ነበረው። ያቀደው ሳይፈጸም ቀርቷል።
የፊልሙ ዘርፍ እየገጠሙት ያሉ ችግሮችን በአጭሩ ለአሜሪካ ድምጽ ያጋራው ሄኖክ፣መንግስት እና ባለሀብቶች በዚህ ወቅት መዝናኛም፣መጽናኛም ሊሆን ሀቅም ያለውን የፊልም ጥበብ ሊደግፉት ይገባል ሲልም ይመክራል።
ከሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረገውን አጭር ቆይታ ያዳምጡ።