በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

«እኔም የደንበኞቼ ዕጣ ቢደርሰኝ ፤ ልጆቼ ምን ይሆናሉ? የሚል ጭንቀት ነበረኝ» የፍራንኮ-ጀርመን ሽልማት አሸናፊ ጠበቃ አምሃ መኮነን


AMEHA MEKONNEN

የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ጠበቃ አምሃ መኮነን የፍራንኮ-ጀርመን ሽልማት ተበረከተላቸው። እኤአ ከ2016 ዓም ጀምሮ መሰጠት የተጀመረው ይህ ሽልማት ፣ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብት ቀንን በማስመልከት የፈረንሳይ እና የጀርመን መንግስታት በጋራ በመሆን ፣ ለሰብአዊ መብቶች መከበር የላቀ እንቅስቃሴ ላደረጉ 15 ግለሰቦች የሚሰጡት ነው ።

ከ100 በላይ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞችን በፍርድቤት ወክለው በመቆም የሚታወቁት ጠበቃ አምሃ ሽልማቱ ጠበቆች ብዙ ጊዜ በማይመርጡት በዚህ ዘርፍ ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግረዋል።

ይህ ሽልማት ለጠበቃ አምሃ መኮነን የተበረከተላቸው ለጋዜጠኞች እና የለውጥ አራማጆችን የገዛ ህይወታቸውን ሳይቀር ለአደጋ አጋልጠው ስለተሞገቱ እንደሆነ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ብሪታ ዋግነር በቲዊተር ገጻቸው ጽፈዋል።

ከጠበቃ አምሃ መኮነን ጋር ሀብታሙ ስዩም ቆይታ አድርጓል።


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG