በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የበረሃ አንበጣ መንጋን ለመከላከል እየተዘጋጀች መሆኑን አስታወቀች


የአንበጣ መንጋ

በአፋር ፣ ሶማሌ፣ ትግራይ ፣ እና አማራ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ ስፍራዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ መታየቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ከአሁን በፊት ለ30 ያክል ጊዜያት ከተለያዩ የአረብ እና አፍሪቃ ቀንድ ሀገራት ተነስቶ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የገባን ሰብል አጥፊ የአንበጣ መንጋ በአውሮፕላን በታጀበ ርብርብ ማስወገዱን ያስታወሱት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዕፅዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘብዴዎስ ሰላቶ ፣አሁን የተሰከሰተውን እና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀውን ፤ ሌላ የወጣት አንበጣ መንጋ በተመሳሳይ ለመከላከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

አቶ ዘብዲዎስ ከኤደን ገረመው ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቆይታ ያዳምጡ፡፡

ኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል እየተዘጋጀች መሆኑን አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG