በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የግልግል ዳኝነቶችን በግዛቷ ከማስፈጸም ምን ታተርፋለች?


በውጭ ሀገራት የሚሰጡ የግልግል ዳኝነቶችን ዕውቅና መስጠት እና ማስፈጸምን በተመለከተ የተደረሰው ስምምነት ይፋ ከተደረገ 60 ዓመታት አልፈዋል።

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ የራሷን አሰራር ከመዘርጋት ውጪ የስምምነቱ ፈራሚ ሆና አልታየችም ነበር።አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያ በውጭ ሀገራት የተሰጡ የግልግል ዳኝነቶችን በሀገር ውስጥ ያለ ተጨማሪ ስነ-ስርዓት እና ቅድመ -ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችላትን ሰነድ ለማጽደቅ እየተዘጋጀች ስለመሆኑ ተሰምቷል።

የኒውዮርክ ኮንቬንሽን የተሰኘው ይሄንን ሰነድ ለመቀበል የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወሰነ ሲሆን ፣ገዥነቱን ለማጽደቅ ደግሞ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀጠሮ እንደያዘለት ተሰምቷል።

ለመሆኑ የሰነዱ ዓላማ ምንድነው? ኢትዮጵያ ሰነዱን በመፈረሟ የምትጠቀማቸው እና የምትጎዳባቸው ጎኖች አሉ ወይ? የሚሉ ጥያቄዎችን አንስቶ ሀብታሙ ስዩም ከባህርዳር ዩኒቨርሰቲው የግብር እና ኢንቨስትመንት ህግ መምህር ምስጋናው ጋሻው ጋር አጨር ቆይታ አድርጓል።

አቶ ምስጋናው የሰነዱን ምንነት እና ይዘት በማስረዳት ይጀምራሉ።


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG