በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"(አርሲ ነገሌ ላይ) አባቴ መግለጽ ከምችለው በላይ በግፍ ተገድሏል" የሟች ሴት ልጅ


አርሲ ነገሌ የሳተላይት ፎቶ
አርሲ ነገሌ የሳተላይት ፎቶ

ለበርካታ ዓመታት በምዕራብ አርሲ ነገሌ ከተማ እንደኖሩ የነገሩን፣ ስማቸው በሚስጢር እንዲያዝ የጠየቁን ነዋሪ ፣የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ መገደል ከተሰማበት ከጥቂት ሰዓታት በኃላ ጀምሮ በከተማዎ አሰቃቂ ግድያ እና የንብረት ዘረፋ መከናወኑን ለአሜሪካ ድምጽ አስረድተዋል።

ሰኞ ሰኔ 22•2012 ንጋት ላይ በተጀመረ "የተደራጀ ጥቃት" በከተማው ውስጥ የሚታወቁ ሰዎችን ጨምሮ -የ3 ሰዎች ህይወት በአንድ ስፍራ ሲጠፋ መመልከታቸውን ግለሰቡ ይናገራሉ።ከእነዚህ መካከል አንዱ አቶ ደነቀው ጉባኤ የተባሉ በነገሌ የሚገኘው የዓለም ሆቴል ባለቤት እንደሆኑም ግለሰቡ አክለው ተናግረዋል።

ከአቶ ደነቀው ልጆች መካከል አንዷን በስልክ አግኝተናል።በሌላ ከተማ ውስጥ ሀዘን ለመቀመጥ የተገደደችው ወጣት “በአባቴ ላይ የተፈጸመውን ግፍ የምንተነፍስበት አጥተን -ግራ ገብቶናል” ትላለች።

ነዋሪው ይሄ ሁሉ በሚፈጸምበት ሰዓት የጸጥታ አስከባሪ አካላት እርምጃ ለመውሰድ አለመቻላቸውን ደጋግመው አንስተዋል። በአንጻሩ የአሮሞ ብሄር ተወላጅ የሆኑ የከተማዎ ነዋሪዎች ፣ ንጹሃንን ከጥቃት ለማዳን ጥረት ሲያደርጉ እንደነበረ ቀደም ብለን ያነጋገርናቸው የከተማዎ ነዋሪ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ከ20 ዓመታት ለሚልቅ ጊዜ በከተማዎ መኖራቸውን የነገሩን አዛውንት በበኩላቸው በዕለቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቆም የተደረገውን ጥረት አውስተው የጸጥታ ሃይል አባላት ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዳቸው “ መደረግ ያልነበረበት እንደሆነ” ያወሳሉ።

ይህ በእንዲህ እያለ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርዶሳ በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች ላይ ጥፋት ያደረሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እያወሉ እንደሆነ እና የደረሰው የጥፋት መጠን በቅርቡ በዝርዝር እንደሚገለጽ ተናግረዋል።

ሀብታሙ ስዩም ዝርዝር ዘገባ አለው።

"(አርሲ ነገሌ ላይ) አባቴ መግለጽ ከምችለው በላይ በግፍ ተገድሏል" የሟች አቶ ደነቀው ጉባኤ ልጅ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:43 0:00


XS
SM
MD
LG