በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ውጥን

ከግራ ወደ ቀኝ የፌዴራል ጠ/ፍቤቶች ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ጠበቃ እና የመብት ተሟጋች ተክለ-ሚካኤል አበበ፣ በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ
ከግራ ወደ ቀኝ የፌዴራል ጠ/ፍቤቶች ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ጠበቃ እና የመብት ተሟጋች ተክለ-ሚካኤል አበበ፣ በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ

ትኩረቱን በህግ የበላይነት መከበር ላይ ያደረገው  የዓለም-ፍትህ መርሃ-ግብር ‘ወርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት’  የተሰኘ ተቋም ህግን በማስከበር እና የህግ የበላይነትን በማክበር ረገድ ሀገራት ያላቸውን ደረጃ ይፋ በማድረግ ይታወቃል፡፡ ዝቀተኛ ደረጃን ካገኙ 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጠቅሷል፡፡

እንዲህ በእየአደባባዩ ሳይቀር በተገቢው የብቃት ደረጃ ላይ አለመገኘቱ የሚጠቀስበትን የፍትህ ስርዓት ለማሻሻል ርምጃዎች እየተወሰዱ ስለመሆኑ ከሰሞኑ በዋሺንግተን ከተማ በተደረገ የማስገንዘቢያ መድረክ ላይ ተወስቷል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ የህግ ባለሙያዎችና ሙሁራን ጋር በመከሩበት በዚህ መድረክ ላይ የኢትዮጵያን የፍትህ ስርዓት የፈተኑ ችግሮች ፣ወደ መፍትሄ አድራሽ ሀሳቦች፣ እንዲሁም የዘመነ ስርዓት አላቸው የሚባሉ ሀገራት ልምዶች ተጋርተዋል፡፡

ሀብታሙ ስዩም የውይይቱን አንኳር ሀሳቦች በቀጣዩ ዘገባው ያስቃኘናል፡፡

ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ውጥን
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:19 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG