በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‹‹ብዙ ጊዜ ፖሊሶች የፈጸሙት ጥፋት እንጂ፣ እነሱ ላይ የተፈጸመባቸው ጎልቶ አይታይም››ኮ/ር ፋሲካ ፋንታው


Addis Ababa police Commission
Addis Ababa police Commission

በማህበራዊ የመገናኛ አውታሮች የተሰራጨ አንድ ቪዲዮ የበርካታ ኢትዮጵያዊያንን ቁጣ ቀስቅሶ ሰንብቷል፡፡

በቪዲዮው ላይ አንድ የአዲስ አበበ ከተማ የፖሊስ ደንብ የለበሰው ግለሰብ፣በካቴና የታሰረን ወጣት ሲደበድብ ፣አንድ እናትን ደግሞ ሲገፈትር ያሳያል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታው ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ሲናገሩ ድርጊቱ ‹‹መላው የፖሊስ አባላትን በማይወክሉ›› የተፈጸመ እና ኮሚሽኑንም ያሳዘነ ነው፡፡ኮሚሽኑ ህዝብን ይቅርታ እንደጠየቀም አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ፣በቀደሙ ጊዜያት ሳይቀር ከህግ አግባብ ውጪ የዜጎችን መብት ይጥሳል በሚል ሲወቀስ ባጅቷል፡፡ኮማንደር ፋሲካ በበኩላቸው የፖሊስ አባላት የሚያጠፉት ጥፋት ጎልቶ የመወሳቱን ያክል በፖሊስ አባላት ላይ የተቃጡ ጥቃቶች እንደማይነገሩ ጠቅሰው ፣ ይሁንና በፖሊስ እና በህዝብ መካከል ያለውን የመፈራራት መንፈስ ለማርገብ እየተሰሩ ያሉ ርምጃዎችን ዘርዝረዋል፡፡

ኮማንደር ፋሲካ ፋንታው ከዘጋቢያችን ሀብታሙ ስዩም ጋር ያደረጉት ቆይታ ከስር ይገኛል፡፡

‹‹ብዙ ጊዜ ፖሊሶች የፈጸሙት ጥፋት እንጂ፣ እነሱ ላይ የተፈጸመባቸው ጎልቶ አይታይም›› ኮ/ር ፋሲካ ፋንታው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:26 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG